Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 07 April 2012 08:08

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ስለ ነፃነት

ነፃነት የማይከፋፈል አንድ ቃል ነው፡፡ ለማጣጣምም ሆነ ልንታገልለት ከፈለግን ለሁሉም ለማዳረስ ዝግጁ መሆን አለብን፡፡ ባለፀጋ ይሁን ድሃ፤ ከኛ ጋር ተስማማም አልተስማማም፤ ዘራቸው ምንም ይሁን ምንም ቢሆን፤ ወይም የቆዳቸው ቀለም…ለሁሉም ልናዳርስ ይገባል፡፡

ዌንዴል ልዊስ ዊልኪ

(አሜሪካዊ ፖለቲከኛና ጠበቃ)

ነፃነት ለማንም ሰው ብድግ ተደርጐ የሚሰጠው ነገር አይደለም፡፡ ነፃነት ሰዎች የሚወስዱትና ያሻቸውን ያህል ነፃ የሚሆኑበት ነው፡፡

ጄምስ ባልድዊን

(አሜሪካዊ ፀሐፊ እና የሲቪል መብት ተሟጋች)

ትግል ህይወቴ ነው፡፡ እስከ ህይወቴ ማብቂያ ድረስ ለነፃነት መታገሌን እቀጥላለሁ፡፡

ኔልሰን ማንዴላ

(ደቡብ አፍሪካዊ ፕሬዚዳንትና ጠበቃ የነበሩ)

ባርያ ጌታውን አይመርጥም፡፡

የአሻንቲዎች አባባል

አገራችን ዓለም ናት፡፡ ህዝባችን የሰው ልጆች በሙሉ ናቸው፡፡

ዊሊያም ሊሎይድ ጋሪሰን

(አሜሪካዊ የፀረ - ባርነት ትግል አራማጅ)

ነፃነት ፈጽሞ ነፃ ሆኖ አያውቅም፡፡

ሜድጋር ኤቨርስ

(አሜሪካዊ የሲቪል መብት መሪ)

በፖለቲካ ውስጥ ሰው የሚያጣው የመጀመሪያ ነገር ነፃነቱን ነው፡፡

ጆኪዩም ማርያ ማቻዶይ አሲስ

(ብራዚላዊ የረዥም ልቦለድ ደራሲና

አጭር ልቦለድ ፀሐፊ)

 

 

Read 2968 times Last modified on Saturday, 07 April 2012 08:12