Sunday, 30 July 2017 00:00

‹‹ኢትዮጵያዊቷ ልዕልትና የቀለበቱ ምስጢር›› ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

 በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ‹‹እንጨዋወት›› በሚል አምዱ ለረዥም ጊዜ የሚታወቀው ደራሲና ተርጓሚ ኤፍሬም እንዳለ “ኢትዮጵያዊቷ ልዕልትና የቀለበቱ ምስጢር›› በሚል ወደ አማርኛ የተረጎመው የአፍሪካ አሜሪካዊው ጆርጅ ሳሙኤል ሹይለር መፅሀፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መፅሀፉ በአምስቱ አመት የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ወቅት በነበሩ ታሪካዊ ክስተቶች መነሻነት የተፃፈ ልቦለድ ሲሆን መረጃ እንደ ልብ በማይገኝበት በዚያ ዘመንና ኢትዮጵያን ረግጦ በማያውቅ ሰው እንዲህ አይነት መፅሀፍ ከተፃፈ ምናልባት እኛ ኢትዮጵያዊያን ያልሰራነው የቤት ስራ እንዳለ አመላካች ነው ብሏል - ተርጓሚው ኤፍሬም እንዳለ፡፡ በ200 ገፆች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ69 ብር ከ90 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 2466 times