Saturday, 22 July 2017 15:51

3ኛው ንባብ ለህይወት የመጻሕፍት ሽያጭና ውይይት ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 የማንበብ ባህልን ለማዳበር ታስቦ በየዓመቱ የሚዘጋጀው 3ኛው ንባብ ለህይወት የመጻሕፍት አውደ ርዕይና የኪነ ጥበብ ድግስ የፊታችን ሐሙስ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይከፈታል፡፡ ለአምስት ተካታታይ ቀናት ለጎብኚዎችና ለመጻሕፍት አፍቃሪዎች ክፍት ሆኖ በሚቆየው በዚህ አውደ ርዕይ ላይ በርካታ መጻሕፍት በቅናሽ ለገዢዎች ለሽያጭ እንደሚቀርቡና በርካታ የመድረክ ዝግጅቶችም እንደሚኖሩ የንባብ ለህይወት አዘጋጆች ገልፀዋል፡፡
 በዘንድሮው የንባብ ለህይወት የመጻሕፍት አውደ ርዕይና የመድረክ ዝግጅት ላይ የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ “የማይፃፍ ገድል”፣ የምስራቅ ተረፈ “ጨው በረንዳ” እና የህይወት ታደሰ “ኀሠሣ” መፅሐፎች እንደሚመረቁም ታውቋል፡፡ በአምስቱም ቀናት የመፅሀፍት አፍቃሪዎች ወደ ኤግዚቢሽን ማዕከል በነፃ በመግባት መጻሕፍትን በቅናሽ መግዛት፣ የተለያዩ ደራሲያንና ጸሐፍት ስራዎቻቸውን ሲያቀርቡ ቀጥታ መታደምና የተለያዩ መዝናኛዎችን መመልከት እንደሚችሉ ተጠቁሟል። በዚህ አውደ ርዕይ ላይ በርካታ አሳታሚዎች፣ አካፋፋዮችና ከህትመት ጋር የተያያዘ ስራ የሚሰሩ ድርጅቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

Read 1040 times