Saturday, 22 July 2017 15:47

የኮንጎው መሪ በ80 ኩባንያዎች ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ አላቸው ተባለ

Written by 
Rate this item
(4 votes)

     70 ሺህ ሄክታር እርሻ እና ከ100 በላይ የአልማዝና ወርቅ ማምረቻ ፈቃድ አላቸው

      የኮንጎው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ እና ቤተሰባቸው በአገር ውስጥና በውጭ አገራት በሚንቀሳቀሱ መሪ ከ80 በላይ ታላላቅ የንግድ ኩባንያዎች ውስጥ ጠቀም ያለ የባለቤትነት ድርሻ እንዳላቸውና አጠቃላይ ሃብታቸው በአስር ሚሊዮኖች ዶላር እንደሚቆጠር ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ተቀማጭነቱ በአሜሪካ የሆነው ኮንጎ ሪሰርች ግሩፕ የተባለው የጥናት ተቋም ያወጣውን የጥናት ውጤት ጠቅሶ ሮይተርስ ከትናንት በስቲያ ባወጣው ዘገባ እንዳለው፣ ጆሴፍ ካቢላ እና ቤተሰባቸው በኩባንያዎቹ ውስጥ ካላቸው የባለቤትነት ድርሻ በተጨማሪ፣ 70 ሺህ ሄክታር የእርሻ መሬትና አልማዝና ወርቅ ማምረት የሚያስችሉ ከ100 በላይ የማዕድን ፍለጋ ንግድ ፈቃዶች አሏቸው፡፡
በ2001 አባታቸውን ተክተው ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ያስታወሰው ዘገባው፣ ምንም እንኳን የስልጣን ዘመናቸው ያበቃው ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ ቢሆንም፣ ስልጣኔን አልለቅም ብለው በመሪነታቸው መቀጠላቸውን አመልክቷል፡፡
በተያያዘ ዜናም በሙስና ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ መዝብረዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸውን የናይጀሪያ የቀድሞ የነዳጅ ሚኒስትር ዲዛኒ አሊሰን ማዱኬ ጉዳይ ሲመረምር የቆየው ፍርድ ቤት፣ የግለሰቧን 37 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈበት እጅግ ዘመናዊ ቤት ሲሆን፣ ለንደን ውስጥ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በዋስ ተፈትተው በዚያው የሚገኙት የቀድሞዋ ሚኒስትር ቤቱን የገዙት ከመንግስት ካዘና ያለአግባብ በመዘበሩት 37.5 ዶላር ነው መባሉን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

Read 3217 times