Print this page
Thursday, 05 April 2012 13:01

“አድማሱ” ፊልም ቀረፃ ሊጀመር ነው

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

‘Don’t Take It’ እየተደመጠ ነው

የኢትዮጵያው ብሉ ናይል ፊልም እና ቴሌቪዥን አካዳሚ እና የስዊዘርላንዱ ቴል (Tele) ፊልም በጋራ የሚያዘጋጁት የ300 ሺህ ዩሮ በጀት ፊልም ቀረፃ በመጪው ሐሙስ በአዲስ አበባ ይጀመራል፡፡በጀቱ ከስዊዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥር የሚገኘው ‘Deza’ ያደረገውን የቁሳቁስ አቅርቦት የሚያካትት ነው፡፡ “አድማሱ” የተሰኘ ርእስ የተሰጠው ፊልም አብዛኞቹ ወጣቶች በሆኑ ባለሙያዎች እና ተዋንያን ይሰራል፡፡

የቀረፃውን መጀመር አስመልክቶ የፊልም እና ቴሌቪዥን አካዳሚው ባለቤት አቶ አብርሃም ኃይሌ ሲናገሩ ልጆቹ ከባለሙያ ጋር በመስራት ልምድ ያገኛሉ ብለዋል፡፡ ለአንድ ወር የሚቆየው ቀረፃ ከስዊዘርላንድ፣ ከጀርመን እና ሌሎች ሀገሮች የመጡ ሳውንድ ኢንጂነሮችና ሌሎች ባለሙያዎች ይሳተፋሉ፡፡

 

በሌላም በኩል ‘Don’t Take It’ የተባለ እና በጣሊያን ሀገር የሚገኝ ኢትዮጵያዊ በእንግሊዘኛ ያወጣው ነጠላ ዜማ በዩቲዩብ ተደማጭነቱ እየጨመረ ነው፡፡ የእውቋ ድምፃዊት ዊትኒ ሂዩስተንን ሞት ተከተሎ አደንዛዥ እፅ አትጠቀሙ የሚል ቅስቀሳ የሚያካሂደውን ነጠላ ዜማ የለቀቀው እስራኤልደ ሊዮኔ ነው፡፡

 

 

Read 1125 times Last modified on Thursday, 05 April 2012 13:03