Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Wednesday, 04 April 2012 11:10

“ስብሃት ገ/እግዚአብሄር ሕይወትና ክህሎት” ለሁለተኛ ጊዜ ታትሞ ወጣ

Written by 
Rate this item
(4 votes)

በሥነፅሁፍ ሃያስያን ዘንድ አነጋጋሪና አወዛጋቢ የነበረው የደራሲ፣ ጋዜጠኛና ሃያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ “ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት” ሂሳዊ መፅሃፍ ሰሞኑን ለሁለተኛ ጊዜ ታትሞ ለገበያ አቀረበ፡፡ መፅሃፉ ለመጀመርያ ጊዜ የተተመው የዛሬ አራት ዓመት ነበር - በ2000 ዓ.ም፡፡ ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ በዚህ መፅሃፍ በዋናነት በስብሃት ሦስት ልብወለዶች ላይ ሂሳዊ ፅሁፍና ትንተና ያቀረበ ሲሆን፤ የስብሃትን ሥራዎች ከበዓሉ ግርማና ሃዲስ አለማየሁ ሥራዎች ጋር እያነፃፀረና እያወዳደረም አቅርቧል፡፡

በዚህም ሁለቱን ፀሃፍት አሳንሶ ስብሃትን ከፍ ከፍ አድርጓል የሚል ትችት ተሰንዝሮበት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ደራሲ ስብሃት መፅሃፉን አስመልክቶ ከቀድሞ ሮዝ መፅሄት ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ “አለማየሁ ገላጋይ ሀዲስ አለማየሁን ማሳነሱ አልታየኝም” በማለት ትችቱን አጣጥሏል፡፡ የደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሐረ ቃለ ምልልስ ተቀንጭቦ በዚሁ በመፅሃፍ ውስጥ እንደተካተተ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 240 ገፆች ያለው መፅሃፉ በ35 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

 

 

 

Read 4771 times Last modified on Wednesday, 04 April 2012 11:12