Wednesday, 04 April 2012 11:01

ፓራሊምፒያኖች በኢትዮጵያ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(2 votes)

ስፖርተኞች የሚለማመዱትና የሚወዳደሩት በማገገሚያ ዊልቼር ነው፤አርቴፊሻል እግሮችና እጆች መጠቀምም አልተጀመረም
የስፖርተኞችን የጉዳት ዓይነተኛ ደረጃ የሚለይ መሳርያ አለመኖሩ ተመጣጣኝ ውድድሮችን ላለማድረግ ምክንያት ሆኗል
የዓለም አቀፍ ውድድሮች ተሳትፎ በሁሉም ደረጃዎች በሚታይ የአቅም ውስንነት አልተጠናከረም
በአቅም ማነስ አስፈላጊ የስፖርት መሳርያዎች ባለመኖራቸው ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራትና ለፓራሊምፒክ የሚያበቃን ሚኒማን ለማሳካት አልተቻለም
በለንደን ፓራሊምፒክ 10 ፓራሊምፕያኖች ለማሳተፍ ታቅዷል፤ለበጀት 5 ሚ. ብር ያስፈልጋል
መስማት ለተሳናቸው ስፖርት ፌደሬሽን ይቋቋማል
የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ በአካል ጉዳተኞች ስፖርት በሚያደርገው እንቅስቃሴ በውድድሮች ብዛትና የስፖርተኞች ተሳትፎ ቢጠናከርም በቂ የፋይናንስ አቅም ባለመኖሩ በተፈለገው መንገድ እንዳይሰራ አድርጎታል፡፡ በለንደን ፓራ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በመወከል ለመሳተፍ 5 ሚሊየን በጀት የሚያስፈልግ ሲሆን 4 አትሌቶች ሚኒማ አሟልተው በውድድሩ ለመሳተፍ እየተጠባበቁ ናቸው፡፡
ከሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት በተካሄደው 3ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ላይ በፓራሊምፒክ ከ9 ክልለሎች የተወከሉ 560 ስፖርተኞች ተሳትፈዋል፡፡  በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ኦሮሚያ በ120 ስፖርተኞች ተሳትፎው ቀዳሚ ነው፡፡ ትግራይ በ80፤ አማራ በ69፤ ደቡብ በ31፤ ስፖርተኞች ተሳትፎ ተከታታይ ደረጃ ነበራቸው፡፡ አፋርና ጋምቤላ አልተካፈሉም፡፡ በ3ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በ3 የውድድር ዓይነቶች ማለትም በጠረጴዛ ቴኒስ፤ በክብደት ማንሳት እና በአትሌቲክስ ከመቼው ግዜ የላቀ ተሳትፎ ተደርጓል፡፡
በፓራሊምፒክ አትሌቲክስ 7 አይነት ውድድሮች አሉ፡፡ ውድድሮቹ የአይነስውራን፤ ዊልቸር ተጠቃሚዎች፤ የእግር ጉዳት፤ የእጅ ጉዳት፤ መስማት የተሳናቸው፤ የአዕምሮ እድገት ችግር  ያለባቸውና በድንክዬዎች  በተከፋፈሉ የአካል ጉዳት ሁኔታዎች  ስፖርተኞችን የሚያሳትፉ ናቸው፡፡ በፓራሊምፒክስ ጠረጴዛ ቴኒስ ያሉት 4 አይነት ውድደሮች ዊልቸር ተጠቃሚዎች፤ የእግር ጉዳት፤ የእጅ ጉዳት፤ መስማት የተሳናቸው ስፖርተኞችን ያሳትፋሉ፡፡  በፓራሊምፒክስ የክብደት ማንሳት ደግሞ 2 አይነት ውድድሮች ዊልቸር ተጠቃሚዎችና የእግር ጉዳት ያለባቸው ስፖርተኞች ይካፈሉበታል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ በፓራሊምፒክ የሚካሄዱ ከ20 በላይ ውድድሮች መኖራቸውን የሚገልፁት አቶ ዮናስ ገ/ማርያም በኢትዮጵያ የፓራሊምፒክ ኮሜቴ የውድድርና ተሳትፎ ስልጠና ባለሙያ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ከላይ በተጠቀሱት 3 የውድድር ዓይነቶች በስፋት እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ በአይነስውራንና የእጅ ጉዳት ባላቸው ስፖርተኞች የጎላ ተሳትፎ መኖሩን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
በፓራሊምፒክና ዓለም አቀፍ ውድድሮች በምናሳትፋቸው ስፖርተኞች ውጤታማነታችን ቢቀጥል ማናጀሮች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የአካል ጉዳተኛ ስፖርተኞችን በመልመል የውድድሮች እድል ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚታመን የገለፁት አቶ ዮናስ መስማት የተሳናቸው ስፖርተኞች ፌደሬሽን የማቋቋም እቅድ ይዘን በ5 ክልሎች ለማዋቀር እንቅስቃሴ እንደተጀመረ፤ ክለቦችን በማቋቋም ስፖርተኞችን ለማብዛት ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ አትሌቶች የፓራሊምፒክ ስፖርተኞች በውድድር ቦታ ተገኝቶ በማነቃቃት እና በአዲስ አበባ ስታድዬም በሚሰሯቸው ልምምዶች አብሮ በመስራት እና ድጋፍ በመስጠት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ይህን ለማጠናከርም ታስቧል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በፓራሊምፒክስ የአትሌቲክስ ውድድር ጥሩ እየተሠራ ነው፡፡ 4 አትሌቶች በለንደን ለሚስተናገደው የ2012 ፓራሎምፒክ የሚያስፈልገውን ሚኒማ አሟልተዋል፡፡ እስከ ነሐሴ ባለው ሚኒማ የማሟያ ጊዜ ተጨማሪ ስፖርተኞች ለፓራሊምፒክ ለማብቃትም ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡ በእጅ ጉዳት የሚካሄዱ የፓራልምፒክ አትሌቲክስ ከ800-1500 ሜትር የሚከናወኑ ውድድሮች አሉ፡፡ በለንደን ፓራሊምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ አትሌቶች 2 ሚኒማቸውን ያገኙት በኒውዝላንድ በተካሄደ የዓለም ሻምፒዮና ነው፡፡ አንደኛው ደግሞ ማፑቶ ሞዛምቢክ ውስጥ ተደርጐ በነበረው የአፍሪካ መላ ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎውን ያረጋገጠ ነው፡፡ ሰሞኑን እየተከናወኑ ውድድሮችም በለንደን ፓራሊምፒክ ተሳትፎ የሚያበቃ ሚኒማ ለማግኘት ኢትዮጵያውያን ስፖርተኞች ተሳትፈው አንዱ አስፈላጊውን ሚኒማ በማምጣት ተሳክቶለታል፡፡
በለንደን ፓራሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያ በ10 የአካል ጉዳት ስፖርተኞች እንድትሳተፍ መታቀዱን የገለፁት አቶ ዮናስ ገ/ማርያም ስፖርተኞቹ በሁለት ጉዳት አይነት በዓይነስውራንና በእጅ ጉዳት ለሚካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች እንዲሳተፉ ጥረት በመደረግ ላይ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በፓራሊምፒክ የስፖርት እንቅስቃሴዎች አስቀድሞ በትግራይ ክልል የተጠናከረ አንቅስቃሴ እንደነበር ያወሱት አቶ ዮናስ በሰሞኑ የኢትዮጵያ መላ ጨዋታዎች ኦሮሚያ በከፍተኛ ደረጃ መጠናከሩን ገልፀው ኦሮሚያ ብዙ አትሌቶችን ለማቅረብ፣ አዳዲስ ስፖርተኞችን በማካተት ጥሩ መስራቱን በመመስከር 120 ስፖርተኞች በመላው ጨዋታዎች በማካፈል ንቁ ተሳትፎ አድርጓል ብለዋል፡፡
ከትግራይ ክልል የሚመጡ የአካል ጉዳተኛ ስፖርተኞች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ባላቸው ልምድ ውጤታማነታቸው እንደተጠበቀ መሆኑንም ሃላፊው ይገልፃሉ፡፡ በተለይ ተስፋ ዓለም ገብሩ የተባለ የትግራይ ክልል አትሌት በኢትዮጵያ የፓራሊምፒክ ስፖርት በመላው የአፍሪካ ጨዋታዎች ሁለት የብርና የነሐስ ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ ፈር ቀዳጅ ታሪክ መስራቱን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ከትግራይ ክልል የተገኙ የአካል ጉዳተኛ ስፖርተኞች ኒውዝላንድ ላይ ተደርጐ በነበረው የዓለም ሻምፒዮና ሁለት የብርና የነሐስ ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ ውጤታማነታቸው መታየቱን ተናግረዋል፡፡
የትግራይ አትሌት ተስፋ ዓለም ገብሩ በለንደን ፓራሊምፒክ ላይ ውጤታማ እንደሚሆን ይጠበቃል ያሉት አቶ ዮናስ በ800፣ በ1500 እና በ5ሺ ሜትር ይሳተፋል ብለው ከ4 ዓመት በፊት በቤጅንግ ፓራ ለምፒክ ኢትዮጵያን ከወከሉ 2 አትሌቶች አንዱ እንደነበረና 4ኛ በመውጣት ዲፕሎማ ማግኘቱን አስታውሷል፡፡
የአካል ጉዳተኞችን በስፖርቱ ለማሳተፍ ከፍተኛ የቅስቀሳ የግንዛቤ ስራዎችን የኢትዮጵያ ስራ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ እያከናወነ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የፓራሊምፒክ ኮሚቴ እንቅስቃሴ የአቅም ውስንነት ዋናው ችግር ሲሆን ብዙ የአካል ጉዳት ስፖርተኞች ኮሚቴ ቢኖሩም እነሱን ወደ ውድድር ቦታዎች ወስዶ ለዓለም አቀፍ ውድድሮች የሚያበቃቸውን ሚኒማ እንዲያገኙ ለማድረግ እንቅፋት አለ፡፡ ሌላው የስፖርቱ ቁሳቁሶች ችግር ነው፡፡ በተለይ ለፓራሊምፒክ ስፖርት የሚሆኑ ዊልቸሮች የሉም፡፡ የኢትዮጵያ የአካል ጉዳት ስፖርተኞች ለዓለምአቀፍ ደረጃ አገልግሎት ላይ በሚውለው ትራይ ሳይክል ዊልቼር ልምምድ አይሠሩም፡፡ ስፖርተኞቹ እየተጠቀሙ ያሉት በሆስፒታል ለማገገሚያ የሚሆነውን መደበኛውን ዊልቼር ነው፡፡ የትራይሳይክል ዊልቼር በዋጋው ከ60-70ሺ ብር ይገመታል፡፡ የኢትዮጵያ ፓራ ሊምፒክ ይህን ዊልቼር ሊገዛ ባለመቻሉ ስፖርተኞች በሆስፒታል በሚሠራበት መደበኛ ዊልቼር እየሠሩና እየተለማመዱ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ስፖርተኞቹ ለተለያየ ውድድር የሚያበቃቸው አስፈላጊውን ሚኒማ በማግኘትና ተገቢው ብቃት እንዳይኖራቸው አድርጓል፡፡ የእግር ጉዳት ያለባቸው የአካል ጉዳት ስፖርተኞች በአርቴፊሻል መሮጫዎች ተገጥሞላቸው እንዲወዳደሩ ማድረግ ቢቻልም ይህ ዓይነቱ ተግባር ገና አልተደፈረም፡፡ በእርግጥ እጅ ጉዳት ያለባቸው ስፖርተኞች ፕሮቴስቲክ የተባሉ አርቲፊሻል እግሮችና እጆች በዓለም ገበያ ከ5ሺ ዶላር ጀምሮ ይገኛል፡፡
ይህን ለማከናወን ግን አሁንም የአቅም ችግር አለ፡፡ የአካል ጉዳት ስፖርተኞችን ያለባቸዉን የጉዳት ደረጃና ዓይነት በመለየት ለመስራት የሚያስችል የአካል በተመጣጣኝ መንገድ ለማወዳደር የሚያግዝ የቴክኖሎጂ መሣርያ ባለመኖሩም ከፍተኛ ችግር አለ፡፡ በፓራሊምፕክ እንቅስቃሴ ያሉትን ችግሮች ለማቃለል በማህበር ደረጀ እየሠራ ያለው ኮሚቴ ራሱን ለመቻል ጥረቱን ይቀጥላል ያሉት አቶ ዮናስ በአገሪቱ ብዙ ውድድሮች ሲኖሩና የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ መጨመር ያሉብንን ችግሮች እንደሚቀረፉ እገምታሁ ብለዋል፡፡ ማህበረሰቡ ለሌላው የስፖርት እንቅስቃሴ የሚያደርገውን ድጋፍ ለእኛም ማድረግ ተገቢ ነው ያሉት አቶ ዮናስ ገ/ማርያም ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ኦሎምፒክ ኮሚቴ የምናገኘው ድጋፍ ዘላቂነት ባለሙ መንገድ መቀየር ይኖርበታል ብለዋል፡፡ ለመለወጠ አያደክመንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ መንግስት ለአካል ጉዳተኞች ኮኔቬሽንስ ለማጽደቅ መነሳቱም ተስፋ ያሳድራል ብለዋል፡፡
የአካል ጉዳት ስፖርተኞች ለሚኖራቸው የውድድር ተሳትፎ ብዙ ተጠቃሚ አይደሉም በአንድ ወቅት በኢንተርናሽናል ውድድር ሜዳልያ ያመጡ አትሌቶች እስከ 30ሺ ብር መሸለማቸው ተስፋ የሚያሳድር ሁኔታ መሆኑን የገለፁት አቶ ዮናስ የአካል ጉዳተኞች በተለያዩ ዓለምአቀፍ ውድድሮች የሚሳተፉበትን ዕድል ለማስፋት ከማናጀሮቹ ጋር የሚሠሩበትን ዕድል ማመቻቸት ብዙም አልተሠራበትም ብለዋል፡፡

Read 4026 times