Monday, 19 June 2017 09:20

የአርቲስት ተስፋዬ አበበና የቴአትር ማዕከላቸው ልደት ይከበራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 የክብር ዶ/ር ተስፋዬ አበበ 78ኛ ዓመት የልደት በዓልና የቴአትር ማደራጃቸው የተመሰረተበት 48ኛ አመት የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል በተለያዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡
በእለቱ ከቴአትር ማደራጃው በወጡ ሙዚቀኞች፣ ተዋንያንና ገጣሚያን ሙዚቃ፣ ግጥምና አጫጭር ድራማ ለታዳሚያን እንደሚቀርብ የክብር ዶ/ር ተስፋዬ አበበ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመስራቹ የሕይወት ታሪክና ማዕከሉ እስከ ዛሬ ያከናወናቸው ስራዎች፣ ለኪነ ጥበቡ ዘርፍ ያበረከታቸው አስተዋፅኦዎችና ወደ ኪነ-ጥበቡ የቀላቀላቸው በርካታ ወጣቶች ለታዳሚ እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡
በልደት በዓሉ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሀላፊዎችን ጨምሮ ከ500 በላይ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ አምባሳደሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የኪነ- ጥበብ አድናቂዎች ይታደማሉ ተብሏል፡፡

Read 1022 times