Monday, 19 June 2017 10:10

“ሀገራዊ ዕሴት እና ንባብ ለሰላም በኢትዮጵያ›› ውይይት ተካሄደ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 “ሀገራዊ እሴት እና ንባብ ለሰላም በኢትዮጵያ” የተሰኘ በንባብ ላይ ትኩረቱን ያደረገ አገራዊ ውይይት ከትላንት በስቲያ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ እስከ እኩለ ቀን በብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፃህፍት ኤጀንሲ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ ውይይቱን ያዘጋጀው የዓለም የእርቅና ሰላም ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡ በዚህ ውይይት ላይ ሰው ከራሱ፣ ከአካባቢው፣ ከፈጣሪው፣ ከተፈጥሮና ከመሰሉ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረው ማንበብ ያለው ፋይዳ ላይ ትኩረት ማድረጉም ተገልጿል፡፡ በውይይቱ ላይ የታሪክ ምሁራን፣ የሰላምና ግጭት አፈታት ተመራማሪዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የተለያዩ የሚኒስትር መስሪያ ቤት ከፍተኛ ኃላፊዎች የሀይማኖት ተቋማት፣ የዕድር መሪዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ሃሳባቸውን አንፀባርቀዋል፡፡

Read 771 times