Sunday, 18 June 2017 00:00

በለንደኑ የመኖሪያ ህንፃ ቃጠሎ፣ 10 ኢትዮጵያውያን የደረሱበት አልታወቀም

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

 17 ሰዎች በሞቱበት የለንደኑ የመኖሪያ አፓርታማ የእሳት አደጋ፤ 10 ኢትዮጵያውያን የደረሱበት አልታወቀም የተባለ ሲሆን እሳቱ የተነሳውም ከአንድ ኢትዮጵያዊ ወጥ ቤት እንደሆነ ተዘግቧል፡፡ ጠፍተዋል የተባሉት ኢትዮጵያውያን በህንፃ ቁጥር 18ኛ እና 19ኛ ወለል ላይ ነዋሪ የነበሩ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ያሉበትን ሁኔታ የሚያውቅ በአቅራቢያው ለሚገኝ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንዲያሳውቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡ በአመዛኙ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሞሮኮ፣ ፊሊፒንስና የምስራቅ አውሮፓ ሀገራት ዜጎች ይኖሩበት እንደነበር በተገለፀው ግሬንፌል ታወር ላይ የእሳት ቃጠሎ ያጋጠመው ማክሰኞ ማታ ሲሆን አንድ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉን አለማቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡
     በለንደን በታክሲ ሹፌርነት የሚተዳደረው ኢትዮጵያዊ በኃይሉ ከበደ፤ በወጥ ቤቱ ውስጥ እሳቱ መቀጣጠሉን ተመልክቶ፣ ጎረቤቶቹ እንዲያመልጡ የማንቂያ ደውል ሲያሰማና በየበራቸው ሲያንኳኳ እንደነበር፣ በዚህም የበርካቶች ህይወት እንዲተርፍ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ዴይሊሜል ዘግቧል፡፡

Read 1614 times