Monday, 12 June 2017 06:45

“የዳንኤል ክብረት እይታዎች›› ብሎግ ሰባተኛ ዓመት ይዘከራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(9 votes)

  ምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን፤ ደራሲና ጦማሪ ዳንኤል ክብረትን “የሰርቆ አደሮች ስብሰባ” የተሰኘውን 7ኛውን የወግ መፅሀፉንና ተወዳጁን “የዳንኤል ክብረት እይታዎች” የተሰኘውን ብሎግ 7ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ማክሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሄራዊ ቴአትር ይዘክራል፡፡  ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ በሰባቱ ወጎች ላይ ፅሁፍ እንደሚያቀርብ የተገለፀ ሲሆን ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፤ “ወጎችና ምልከታቸው” በሚል ርዕስ ፅሁፍ ያቀርባል ተብሏል፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ዲስኩር፣ አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያምና ዓለማየሁ ታደሰ የተመረጡ ወጎችን የሚያቀርቡ ሲሆን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችን እንደሚያነሳና ዝግጅቱ በመሶብ የባህል ሙዚቃ ቡድን እንደሚታጀብ ምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አስታውቋል፡፡

Read 7269 times