Sunday, 21 May 2017 00:00

ጣሊያን የዓለማችን ቁጥር አንድ ጤናማ አገር ናት ተባለ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

     ሰሞኑን ይፋ የተደረገው የአመቱ የብሉምበርግ አለማቀፍ የጤና ሁኔታ አመላካች ሪፖርት፣ ጣሊያንን ከዓለማችን አገራት እጅግ ጤናማዋ በሚል በአንደኛ ደረጃ ላይ ማስቀመጡን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡
በ163 የዓለማችን አገራት ላይ የተሰራው የጤና ሁኔታ አመላካች ጥናት ሪፖርት፣ ጣሊያን በተለያዩ የጤና መስፈርቶች መሰረት ከአለማችን አገራት በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የገለጸ ሲሆን በአገሪቱ አማካይ ዕድሜ ከፍተኛ መሆኑን፣ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች አቅርቦትም ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱንና ጤናማ አመጋገብ መኖሩን አስታውቋል፡፡
በዘንድሮው የብሉምበርግ የዓለማችን አገራት የጤና ሁኔታ ሪፖርት መሰረት፣ በጤናማነት ከጣሊያን በመቀጠል በቅደም ተከተላቸው እስከ አምስተኛ ደረጃን የያዙት አገራት አይስላንድ፣ ስዊዘርላንድ፣ ሲንጋፖርና አውስትራሊያ መሆናቸውንም  ዘገባው ገልጧል፡፡

Read 2964 times