Saturday, 20 May 2017 13:09

ጥንዶቹ ድምጻውያን ወደ ቢሊየነርነት ተሸጋግረዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የቢዮንሴ እና የጄይ ዚ ሃብት 1.16 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል
     በቅርቡ መንታ ልጆችን ወልደው ለመሳም እየተዘጋጁ የሚገኙት አሜሪካውያኑ ድምጻውያን ቢዮንሴ ኖውልስ እና የትዳር አጋሯ ጄይ ዚ ከሚሊየነርነት ወደ ቢሊየነርነት መሸጋገራቸውን የዘገበው ፎርብስ መጽሄት፣ የጥንዶቹ የጋራ ሃብት 1.16 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን አስታውቋል፡፡
የጄይ ዚ የተጣራ ሃብት 810 ሚሊዮን ዶላር መድረሱንና የባለቤቱ ቢዮንሴ ሃብት በበኩሉ 350 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን የጠቆመው ፎርብስ፤ ጥንዶቹ ወደ ቢሊየነርነት ያሸጋገራቸውን አብዛኛውን ሃብት ያፈሩት በሮክ ኔሽን እና በሌሎች የጄይ ዚ ትርፋማ ኩባንያዎች አማካይነት እንደሆነም ገልጧል፡፡
በትዳር ቆይታቸው የአምስት አመት ሴት ልጅ ያፈሩት ጥንዶቹ፣ በታዋቂው ታይዳል ኩባንያ ውስጥ ጠቀም ያለ የሃብት ድርሻ እንዳላቸው የጠቆመው ፎርብስ መጽሄት፤ ጄይ ዚ ባለፈው ሳምንት ላይቭ ኔሽን ከተባለው ታዋቂ ኩባንያ ጋር ለ10 አመታት የሚቆይና 200 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት አዲስ ውል መፈጸሙንም አስታውሷል፡፡

Read 1631 times