Sunday, 30 April 2017 00:00

አሜሪካ ዜጎቿ ወደ ጎንደር እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(13 votes)

     7ኛው የከተሞች ፎረም ቀን በጎንደር እየተከበረ ነው
የአሜሪካ መንግሥት በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በአንድ ወር ውስጥ 4 ጊዜ ያህል በሆቴሎችና መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የፈንጂ ጥቃት መድረሱን በመጥቀስ፤ ዜጎቹ ወደ ከተማዋ ጉዞ እንዳያደርጉ አስጠነቀቀ፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ ጠቅሶ፤ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) እንደዘገበው፤ በዚህ ወር በከተማዋ 4 ያህል ፍንዳታዎች መከሰታቸው ማስጠንቀቂያው መነሻ ሆኗል ተብሏል፡፡
ኤምባሲው በመግለጫው፣ አሜሪካውያን ወደ ጎንደር ስለሚያደርጉት ጉዞ ደግመው ደጋግመው እንዲያስቡበት ጠቁሞ፣ በአሁኑ ወቅት የያዙት የጉዞ እቅድ ካላቸውም እንዲሰርዙ አሳስቧል፡፡ በሌላ በኩል ጎንደር ከዛሬ ጀምሮ 7ኛውን የከተሞች ፎረም ቀን እያከበረች ሲሆን በዓሉ ለአንድ ሳምንት እንደሚቀጥል ከከተማዋ ከንቲባ ቢሮ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።
በ2008 የክረምት ወራት በጎንደር ከተማ የተነሱ የህዝብ ተቃውሞዎችን ተከትሎ በተከሰቱ ግጭቶች በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጥፋትና ጉዳት መድረሱ አይዘነጋም፡፡

Read 6754 times