Monday, 27 March 2017 00:00

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የዓለም የቴአትር ቀንን በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች ያከብራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የዓለም የቲያትር ቀንን በተለያዩ የኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች ያከብራል፡፡ ዛሬ ጠዋት በሚከፈተው በዚህ የኪነ - ጥበብ ዝግጅት ላይ በአገራችን ቴአትር ላይ ያተኮሩ 8 ጥናታዊ ፅሁፎች፣ በርካታ ቴአትሮች፣ መነባንብና የተለያዩ የስነ - ፅሁፍ ውጤቶች ለታዳሚው እንደሚቀርቡ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ ህዝብና ዓ ለም ግ ንኙነት ዳ ይሬክተር አቶ አስተዋይ መለሰ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
   በዝግጅቱ ላይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከጎንደር፣ ወሎ፣ መቀሌ፣ አዲግራት፣ አክሱም፣ ጂማና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴአትር ዲፓርትመንት የሚመጡ መምህራንና ተማሪዎች የሚታደሙ ሲሆን የጎንደር፣ የወሎና የጂማ ዩኒቨርስቲ የቴአትር መምህራንና ተማሪዎች የየራሳቸውን ቴአትር ለእይታ እንደሚያቀርቡም አቶ አስተዋይ ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ‹‹የቃቄ ወርዲዮት›› ን፣ የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ‹‹እንግዳ›› ቴአትርን በማቅረብ የበዓሉ ተሳታፊዎች ይሆናሉ ተብሏል፡፡ የበዓሉ አዘጋጅ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው እንደሆነ የሚነገርለትን ‹‹የአውሬዎች መሳለቂያ ኮሜዲያ” የተሰኘ ቴአትር፣በቴአትር መምህራንና ተማሪዎች ለእይታ እንደሚያቀርብም ታውቋል፡፡ ከዛሬ ጠዋት አንስቶ እስከ ሰኞ ማታ በሚዘልቀው በዚህ የቴአትር ክብረ በዓል ላይ፣ በወሎ ባህል ላይ ጥናት ተደርጎ የተሰራ ‹‹ፋቂዎቹ” የተሰኘ ቴአትርና በጋሞ ባህል ላይ የሚያጠነጥን “ጋሞታ ወጋ” የተሰኘ ቴአትር ለታዳሚዎች ይቀርባሉም ተብሏል፡፡

Read 1432 times