Saturday, 18 March 2017 15:37

“ፖለቲካ-ኢኮኖሚና የኢትዮጵያ ህዳሴ” ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ጽ/ቤት ሀላፊ በሆኑት አቶ ዓለምነው መኮንን የተፃፈውና የልማትና የዴሞክራሲ አማራጭ አስተሳሰቦች መዋቅራዊ ለውጥና ማህበራዊ ካፒታል ላይ የሚያጠነጥነው ‹‹ፖለቲካ- ኢኮኖሚና የኢትዮጵያ ህዳሴ›› መፅሐፍ ዛሬ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ይመረቃል፡፡በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የብአዴን ሊቀመንበርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ወ/ማርያምና በርካታ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች የሚገኙ ሲሆን ደራሲ አበረ አዳሙ፣ የቀድሞየህንድ አምባሳደር ወ/ሮ ገነት ዘውዴና አርቲስት ተስፋዬ ማሞ በመፅሐፉ ላይ ለውይይት መነሻ የሚሆኑ የዳሰሳ ፅሁፎችን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ በአራት ምዕራፎችና በስድስት ክፍሎች የተዘጋጀው መጽሐፉ፤ በ433 ገጾች ተቀንብቦ በ129 ብር ከ90 ሳንቲም ለአገር ውስጥ፣በ24.90 ዶላር ለውጭ አገራት ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 1011 times