Saturday, 18 March 2017 15:40

ዛሬ የሚመረቁ መጻሕፍት

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 “ከምባታነት፡ እሴቶቹ፣ ትምህርትና ልማት” ዛሬ ይመረቃል

       በደራሲ ብርሃኔ ፈለቀ የተጻፈውና በከምባታ ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥነው “ከምባታነት፡ እሴቶቹ፣ ትምህርትና ልማት” የተሰኘ መፅሐፍ ዛሬ ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ መገናኛ በሚገኘው ብሉ ስካይ ሆቴል ይመረቃል፡፡ መፅሐፉ በከምባታ ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ እንደሚያጠነጥን የጠቆሙት ደራሲው፤ትምህርት ለከምባታ ህዝብ
ያለው ጠቀሜታ፣ከአካባቢው በየጊዜው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረገው ፍልሰት እና በአጠቃላይ የአካባቢው መሰረተ ልማትና ባህላዊ እሴት የሚሉ እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ደራሲያን፣ሀያሲያን፣ የከምባታ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ደራሲው በ2006 ዓ.ም “ወጣቱና 21ኛው ክፍለ ዘመን” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ ያበቁ ሲሆን በፍልስፍና ዲፕሎማ፣ በነገረ መለኮት የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በማኔጅመንትና ሊደርሺፕ ሁለት የማስተርስ ድግሪዎች እንዳላቸው ተጠቁሟል፡፡ ላ ለፉት 1 1 ዓ መታትም የ ወጣቶች
የምክር አገልግሎት በመስጠት ሲሰሩ እንደቆዩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 918 times