Monday, 13 March 2017 00:00

ኢትዮ - ቴሌኮም የሞባይል ተጠቃሚዎች 51 ሚሊዮን ደርሰዋል አለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 ከፍተኛውን ገቢ የማገኘው ከሞባይል ደንበኞቹ ነው
                                
      ኢትዮ-ቴሌኮም አጠቃላይ የሞባይል ስልክ ደንበኞቹን ብዛት ወደ 51 ሚሊዮን ማሳደጉንና ይህም ከአጠቃላይ ገቢው 74 በመቶ በላይ እያስገኘለት መሆኑን አስታውቋል፡፡
ተቋሙ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ፤ አጠቃላይ የደንበኞቹን ቁጥር ወደ 52.9 ሚሊዮን ማሳደጉንና ከነዚህ ውስጥ 51 ሚሊዮን ያህሎቹ የሞባይል ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ጠቁሞ፤ ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የደንበኞቹ ቁጥር በ11 በመቶ መጨመሩን አስታውቋል፡
የኢንተርኔት ዳታ ተጠቃሚዎች ቁጥርም ካለፈው ዓመት የ7 በመቶ እድገት አስመዝግቦ ወደ 14.5 ሚሊዮን መድረሱን አስታውቋል፡፡
ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከደንበኞቹ 15.64 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን የጠቆመው ተቋሙ፤ ይህም ካለፈው አመት ገቢውን ሲነፃፀር የ17 በመቶ እድገት አሳይቷል ብሏል፡፡
ደንበኞቼን በአገልግሎቴ እያረካሁ መሆኑን ያደረኩት ጥናት ጠቁሞኛል ብሏል ኢትዮ - ቴሌኮም።
ከአጠቃላይ የተቋሙ ገቢ ውስጥ ከሞባይል አገልግሎት ያገኘሁት ከአጠቃላይ ገቢው 74.5 በመቶ ሲሆን ከኢንተርኔት 14 በመቶ እንዲሁም ከአለማቀፉ አገልግሎት 7 በመቶ ገቢ ነው ብሏል ድርጅቱ፡፡

Read 1328 times