Print this page
Monday, 13 March 2017 00:00

በ2009 ኮፓ ኮካ ኮላ 36ሺ ታዳጊዎች ይሳተፋሉ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(2 votes)

  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከኮካ ኮላ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሚያካሂደው የ2009 ኮፓ ኮካ ኮላ  ላይ እድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሚሆናቸው 36ሺ ታዳጊዎች እንደሚሳተፉ ታወቀ፡፡ የእግር ኳስ ውድድሩ በመጋቢት ወር አጋማሽ ላይ የሚጀመረው በ1000 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ 36ሺ ተማሪዎች  በየትምህርት ቤታቸው በሚያደርጉት ውድድር ሲሆን፤ ከዚያም በከተማና በክልል መስተዳድሮች ደረጃ ፉክክሮች ይቀጥሉና  መጨረሻው  በክልልና ከተማ መስተዳደሮች ተወካዮች መካከል የሚካሄደው አገር አቀፍ ውድድር ይሆናል፡፡
ኮፓ ኮካ ኮላ በእግር ኳስ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊዎች በቅርበት ተከታትሎ ለመመልመል አመቺ  መድረክ እየሆነ መጥቷል፡፡ በየዓመቱ ከውድድሩ ጋር ተያይዞ በሚደረጉት እንቅስቃሴዎች በዋና አጋርነት ከሚሰሩት ኮካ ኮላ ኢትዮጵያ እና የእግር ኳስ ፌደሬሽኑ ባሻገር የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ፤ የትምህርት ሚኒስቴር፤ የክልልና የከተማ መስተዳደሮች እንዲሁም የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሌሎቹ ባለድርሻ አካላት ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በታዳጊና ወጣት የእድሜ ደረጃዎች እግር ኳሱን በመምራት አበረታች እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፤  በኮፓ ኮካኮላ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊዎች ከወጣቶች አካዳሚው ጋር በመሆን እየመለመለም ይሰራል፡፡ ከ15 በታች የሚካሄደው ኮፓ ኮካ ኮላ ካፕ በእግር ኳስ ፌደሬሽኑ ከ17 ዓመት በታች እና ከ20 ዓመት በታች ለሚደረጉት ውድድሮች ተተኪ ተጨዋቾችን በማቅረብ ልዩ ግብዓት እየሆነ ይገኛል፡፡ በ2009 የኮፓ ኮካኮላ ማጣቃለያ ለተወሰኑ ታዳጊዎች በወጣቶች የስፖርት አካዳሚ የመሰልጠን እድል እንደሚኖርም ታውቋል፡፡

Read 1295 times