Sunday, 26 February 2017 00:00

በደቡብ አፍሪካ በስደተኞች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት አገርሽቷል

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(13 votes)

  በስደተኞች ላይ ያለ ጥላቻን ለመግለፅ ታስቦ ከትናንት በስቲያ በፕሪቶሪያና አካባው ሊደረግ ታቅዶ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍን መከልከል
ተከትሎ፣ በደቡብ አፍሪካ አንዳንድ አካባቢዎች በስደተኞች ላይ ጥቃት ማድረስ ተጀምሯል፡፡
    የተቃውሞ ሰልፉን የጠራው የማሚሎዲ ማህበረሰብ፤ በአገሪቱ የሚገኙ ስደተኞች ላይ ያለውን ለመግለፅና ስደተኞቹ ከአገሪቱ እንዲወጡ ለማድረግ የሚያስችል የተቃውሞ ድምፁን ለማሰማት ነበር።ሰልፉ በአገሪቱ መንግስት ፍቃድ በመከልከሉ ምክንያት ጥቃት ማድረስ መጀመሩን ከደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ እስከአሁን ድረስ በዜጎች ላይስለደረሰው ጉዳት ግን የተገለፀ ነገር የለም፡፡

Read 4630 times