Sunday, 19 February 2017 00:00

‹‹የእግዜር ድርሰት›› ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በደራሲ ይባቤ አዳነ (ግሩም ጥበቡ) የተፃፈው ‹‹የእግዜር ድርሰት›› የተሰኘ መጽሐፍ ሰሞኑን ገበያ ላይ ዋለ፡፡ ትኩረቱን በጥበብ ላይ አድርጎ የተዘጋጀው መፅሐፉ፤በተለይ ኢትዮጵያ ከ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ ጥበብና
ጥንቆላን አደበላልቃ እየደቆሰች የሄደችበትንና የወላድ መኻን የሆነችበትን ሁኔታ ያሳያል። በተጨማሪም የጥበብና የጥንቆላን ልዩነት ለማሳየት፣ ለፍቶ አዳሪው ወገን ወጥቶ ወርዶ፣ በድካም ካመረተው ምርትና ካቀረበው ማዕድ፣
ከሩቅ ሀገር እጁን እየሰደደ መና የሚያስቀረውን አሰራር ለመከላከልና መጠበቂያውን ለማስታጠቅ ብሎም ጥብብ ለጥቂቶች ብቻ የተቸረች አለመሆኗን ለማስገንዘብ ታልሞ የተሰናዳ ነው ብሏል - ደራሲው በመግቢያው ባሰፈረው
ጽሁፍ፡፡    የደራሲው አራተኛ ስራ የሆነው ‹‹የእግዜር ድርሰት››፤ በ196 ገጾች ተቀንብቦ፣ በ61 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም ‹‹አክሳሳፎስ››፣ የከተማው አህያ›› እና ‹‹ስልጡን ድንቁርና›› የተሰኙ መጻህፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡

Read 3019 times