Saturday, 18 February 2017 12:27

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ምንም ዓይነት የቪዛ እገዳ አላደረኩም አለች

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(7 votes)

የተለመደው የቪዛ አሰጣጥ ሂደት ይቀጥላል ተብሏል

የአሜሪካ መንግስት ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት በኢትዮጵያውያን የቪዛ አሰጣጥ ሂደት ላይ ለውጥ መደረጉንና እገዳ እንደተጣለ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን የገለፀው የአሜሪካ ኤምባሲ፤ የተለመደው የቪዛ አሰጣጥ ሂደት ይቀጥሏል ብሏል፡፡
የቪዛ ማደሻ ጊዜው ካለፈ ከ12 ወራት በታች የሆናቸው አመልካቾች ለቃለመጠይቅ ሳይቀርቡ ቪዛ እንዲታደስላቸው ዳግም ማመልከት እንደሚችሉ የጠቆመው ኤምባሲው፤  የተለመደውን የደህንነት ፍተሻ ግን የግድ ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፤ እንደአስፈላጊነቱ ከቆንስላ መኮንን በሚቀርብ ጥያቄ መሰረትም ለቃለመጠይቅ የሚቀርቡበት ሁኔታ እንደሚኖር አመልክቷል፡፡
ዕድሜያቸው ከ14-79 የሆነ አመልካቾች፤ ከአንዳንድ የቪዛ አይነቶች በስተቀር በአካል በመገኘት ማመልከት እንደሚገባቸው የሚገልፀው የኤምባሲው መረጃ አሠራሩም ቀደም ሲል በነበረበት ሁኔታ፤ እንደሚቀጥል አስታውቋል በአሜሪካ ፍርድ ቤት የተላለፈው የእግድ ውሳኔ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ተቀባይነት ያለው በመሆኑ በአስፈፃሚው ትዕዛዝ ዕገዳ የተጣለባቸው የሰባቱ አገራት ዜጎች በተለመደው የቪዛ አሰጣጥ ሥርዓት ማመልከት እንደሚችሉና የእገዳ ትዕዛዙ ኢትዮጵያውያንን የማይመለከት መሆኑን የኤምባሲው መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

Read 3242 times