Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 March 2012 10:21

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(7 votes)

ይህን ሁሉ ነፃነት

ይህን ሁሉ ቀለም

ለትንሽ ወፍ ሰቶ

ባሳብ የሚያስተኛኝ

አድክሞ የሚያስተኛኝ

ሃሳብ አጣሁና

አንድ ህልም አለምኩኝ

እኔው ፈጠርኩና

የፈጠርኩት ህልሜ

ህልሜን ሳስብ

ባሪያው እያረገኝ

ፈጥሬ ባለምኩት

ሲወስድ ሲፈታኝ

ህልሜ የሚያስፈራው ህልሜን

ፈጥሬ ስፈራ ይኸው አሳተኝ

ስፈራ ስፈራ

ይኸው እስካሁን አለሁ

የኔን ህልም ስፈራ

ምን አልባትም መኖር

ምን አልባትም ህይወት

እንደመጠናችን

እንደጀልባ ሰርተን

እኛው እምንቀዝፋት

በደመናው ብዛት

በሰማይ ስፋት

በዛፉ ቅርንጫፍ

ወፍ በምትበርበት

እሄዳለሁ የትምአገኘሁ

ሠፊ ምርጫ በማላውቀው ቦታ

አቅጣጫ እመርጣለሁ

ስሜን እስክረሳ

ማረፊያዬ ሆነው

ሌሎች ተፈጥሮዎች

እንደታፈነ ጭስ

ቀዳዳ እንዳገኘ

ቦታ እንደማይመርጠው…

ገጣሚና ደራሲ መስፍን ኃ/ማርያም

 

 

Read 5523 times Last modified on Saturday, 17 March 2012 10:23