Saturday, 11 February 2017 13:18

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

ESOG) 25ኛ አመት የብር ኢዮቤልዩ በአሉን አከበረ
                    • ደም በመለገስ ምክንያት እናትን ከሞት አተረፈ ማለት ሐገር አተረፈ ማለት ነው፡፡
                    • በኢንክፌክሽን እና በመሳሰሉት እናቶች ለመሞት ከ3-5 ቀን ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡
                    • በደም መፍሰስ ምክንያት ለመሞት ግን እናቶች የሁለት ሰአት ብቻ ጊዜ ይኖራቸዋል፡:
                                                         / ሠሃሑ

       ደም በመለገስ ምክንያት እናትን ከሞት አተረፈ ማለት ሐገር አተረፈ ማለት ነው፡፡
በኢንክፌክሽን እና በመሳሰሉት እናቶች ለመሞት ከ3-5 ቀን ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡
በደም መፍሰስ ምክንያት ለመሞት ግን እናቶች የሁለት ሰአት ብቻ ጊዜ ይኖራቸዋል፡:
/  ሠሃሑ
ባሳለፍነው ሳምንት ጥር 25-27 የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በአዲስ አበባ በካፒታል ሆል የ25ኛውን አመት የብር ኢዮቤልዩ በአል እና አመታዊ ጉባኤውን እንዲሁም የአፍሪካ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ፌደሬሽን 2ኛው አመታዊ ጉባኤ ተካሂዶአል፡፡  
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከተቋቋመ ዘንድሮ 25ኛ አመት የሞላው ሲሆን መሪ ቃሉም  SDG: opportunity and challenges for RH in Africa / በአፍሪካ ዘላቂ የልማት ግብ ለስነተዋልዶ ጤና መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮት/ የሚል ነበር፡፡ እንደ ዶ/ር ደረጀ ንጉሴ የማህበሩ ፕሬዝዳንት አባባል መሪ ቃሉ በአለም አቀፍ ደረጃ በዘላቂው የልማት ግብ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን መልካም አጋጣሚዎቹን በመጠቀምና ችግሮቹን በመለየት ማህበሩም በዚህ ረገድ የሚኖረውን ድርሻ ለመወጣት እንዲያስችለው የታሰበ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር 25ኛ በአልና አመታዊ ጉባኤ እንዲሁም የአፍሪ ካው የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ፌደሬሽን 2ኛ አመታዊ ጉባኤ ለ3/ቀናት ሲካሄድ በድምሩ ወደ 70/የሚደርሱ ጥናታዊ እና ሳይንሳዊ ወረቀቶች በባለሙያዎች ቀርበው ነበር፡፡ ተሰብሳቢዎቹም ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከአፍሪካና ከተለያዩ የአለም ክፍሎች ተዳምሮ  ከ300/ሶስት መቶ በላይ የሚደርሱ ነበሩ፡፡
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር 25ኛ አመት በአል ከመጀመሩ አስቀድሞ በነበሩ ቀናት የህክምና ባለሙያዎች ተከታታይ ትምህርት በሚለው ፕሮግራም በማህበሩ የስብሰባ አዳራ ሽና በፓውሎስ ሆስፒታል እንዲሁም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፣ በካፒታል ሆል ፣በኢትዮ ጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር አባላት እንዲሁም በአሜሪካ የጽንስና ማህጸን ኮሌጅ እና ሌሎች ተባባሪ አካላት ለማህበሩ አባላት ስልጠና ተሰጥቶአል፡፡
የሳይንሳዊ ወረቀቶቹ አቀራረብ የተጀመረው SDG: opportunity and challenges for RH in Africa / uአፍሪካ ዘላቂ የልማት ግብ ለስነተዋልዶ ጤና መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮት በሚለው ርእስ ሲሆን ከአቅራቢዎቹም ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወትና ዶ/ር አዝማች ሐዱሽ ከአለም የጤና ድርጅት ይገኙበት ነበር፡፡
ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት በዘንድሮው የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በስራ ዘመናቸው የእናቶችን ሕይወት በማዳን እና ባለሙያዎችን በማፍራት እንዲሁም ከሙያቸው ጋር በተያያዘ የተለያዩ ሳይንሳዊ ምርምሮችን በማቅረብ እና ከሙያቸው ጋር በተያያዘ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች እና በኢትዮጵያ ጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ባደረጉት አስተዋጽኦ ተሸላሚ ከሆኑት ባለሙያዎች አንዱ ናቸው፡፡ ዶ/ር ይርጉ የአፍሪካው የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ፌደ ሬሽን የመጀመሪው ፕሬዝዳንት የነበሩ ሲሆን እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፉ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ፌደሬሽን ውስጥ ካሉት 6/ኦፊሰሮች አንዱ በመሆን በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ ዶ/ር ይርጉ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘርፉ መምህር ናቸው፡፡  
የእናቶች ሞት በአፍሪካ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ለሚለው ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት ተከታዩን መልስ ሰትተዋል፡፡
“...የምእተ አመቱ የልማት ግብ በ2015/ ከተጠናቀቀ በሁዋላ ተከታይ የሆነው ቀጣይነት ያለው የልማት ግብ የሚል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ያለውን የእናቶች ሞት ቁጥር ብንመ ለከት በአማካይ ወደ 44 % ያህል የቀነሰ ሲሆን በዚህም ስሌት መሰረት በፊት የነበረው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የነበረው የእናቶች ሞት አሁን ወደ 303/ሶስት መቶ ሶስት ሺህ አካባቢ ይደ ርሳል፡፡ ይህ ሲባል ግን አሁንም 99/% የሚሆነው የእናቶች ሞት ያለው በማደግ ላይ ባሉ ሐገራት ነው። አብዛኛው ማለትም ወደ 2/3ኛው የእናቶች ሞት የሚኖረው ደግሞ ከሰሐራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሐገራት መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ ስለዚህም በቀረበው ወረቀት ላይ ምን ችግር አለ? ምንስ መልካም አጋጣሚ ይኖራል ?የሚለውን ለማየት ተሞክሮል፡፡ ቀጣይነት ያለው የልማት ግብ አላማው የእናቶችን ሞት አሁን ካለበት ደረጃ ዝቅ ወዳለ ቁጥር ማውረድ ሲሆን ይኸውም አሁን በአለም ደረጃ ያለው የእናቶች ሞት በ100000 በሕይወት ከሚወለዱ ወደ 210/ሲሆን ይህንን ወደ 70% ለመቀነስ ነው፡፡ ከዚሁ ጎን ኢትዮጵያ ያመጣችውን ለውጥ ለማየት የተሞከረ ሲሆን ያሉት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ የእናቶች ሞት ከነበረበት ሁኔታ ወደ 72 % ቀንሶአል፡፡ ይህም ኢትዮጵያን የሚያስመሰግንና ከፍተኛ ውጤት ነው፡፡ ምክንያቱም ሌሎች የአፍሪካ ሐገራት የእናቶች ሞት በምንም ሁኔታ ያልቀነሰባቸው ስላሉ ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል ሁለቱም ኮንጎዎች እንዲሁም ሴራሊዮን ምንም ለውጥ የሌለበት እና የእናቶች ሞት ያልቀነሰባቸው ሐገራት ሲሆኑ ዚምባቡዌ ላይ ከመቀነስ ወይንም ቀድሞ ከነበረበት ቁጥር ከመውረድ ይልቅ እንዲያውም የመጨመር አዝማሚያ የታየበት ሁኔታ ይታያል፡፡ ስለዚህም የእናቶችን ሞት ማስቀረትን በሚመለከት መጠነኛ ለውጥ፣ ዝቅተኛ ለውጥ ፣ከፍተኛ ለውጥ እና የምእተ አመቱን የልማት ግብ ያሳኩ ሐገራት ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያም ያደረገችው መሻሻል ከፍተኛ ለውጥ አሳይተዋል ከሚባሉት ሐገራት መክከላ ነው፡፡”
ለእናቶች ሞት ምክንያት የሚባሉት ችግሮችና ያንን ለማሻሻል መልካም አጋጣሚ የሚባለው ምንድነው? ዶ/ር ርጉ ገ/ሕይወት እንደሚከተለው አብራርተዋል፡፡
“... ለእናቶች ሞት ምክንያት የሚባሉ ብዙ ችግሮች ያሉ ሲሆን በተለይም በተወሰኑ የአፍሪካ ሐገራት ውስጥ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ወይንም ያለመኖር፣ በየጊዜው የሚከሰቱ አዳዲስ ተላላፊ በሽታዎች ይህም ማለት የጤና ሲስተሙን የሚያናጋና ባለሙያዎችንም ለአደጋ የሚያጋልጡ እንደኢቦላ ያለውን ማለት ነው፣ ስራው ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ የሚፈልግ ሲሆን የገንዘብ እጥረትም ሌላው ችግር ነው፡፡ ከዚህ በፊት ሴቶች የሚሞቱባቸው ምክንያቶች እየተቀየሩ ሌሎች አዳዲስ ምክንያቶች እየተገኙ ስለሚመጡ ያንን አውቆ ክትትል ማድረግና እልባት መስጠት ያስፈልጋል፡፡ እንደዚህ ያሉት ነገሮች ለወደፊቱም በአፍሪካ ለመጪው ጊዜም ፈታኝ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል፡፡”
ዶ/ር አዝማች ሐዱሽ የአለም ጤና ድርጅት ውስጥ ይሰራሉ፡፡ የጽንስና ማህጸን ሐኪምና የህብረተሰብ ጤና እስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር አዝማች ሐዱሽ SDG: opportunity and challenges for RH in Africa / በአፍሪካ ዘላቂ የልማት ግብ ለስነተዋልዶ ጤና መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮት በሚለው ርእስ ስር ያቀረቡትን ሳይንሳዊ እውነታ እንደሚከተለው አብራርተዋል፡፡
“...እንደሚታወቀው የእናቶች ሞት በኢትዮጵያ የጤና ሴክተር ይሁን በማንኛውም ተመሳሳይ መስሪያ ቤት ዋና አጀንዳ ነው፡፡ አንድም እናት በወሊድ ምክንያት መሞት የለባትም የሚለው በሁሉም ዘንድ የሚታሰብና ለዚህም አስፈላጊው እንዲተገበር የሚፈለግ ሲሆን በቅድሚያ ግን መተግበር ያለበት ነገር እናቶች በምን ምክንያት ይሞታሉ? የሚለውን በእርግጠኝነት ማወቅ ነው፡፡ ስለዚህም ከሌሎች ሐገሮችም ይሁን ከኢትዮጵያ የተገኙት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እናቶች በአብዛኛው የሚሞቱት በደም መፍሰስ መሆኑ ተረጋ ግጦአል፡፡ መድማት የሰው ሕይወት ሊቀጥፍ አይገባም የሚለው ቢያስማማም በአለም 1/3ኛ የሚሆኑት በኢትዮያ ደግሞ ወደ 50% የሚሆኑት እናቶች የሚሞቱት በመድማት ምክንያት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል ለእናቶች ሞት ምክንያት የነበሩት አሁንም አሉ ቢባልም በእጅጉ የቀነሰ ሲሆን በመድማት ምክንያት የሚሞቱት እናቶች ግን ቁጥራቸው አሁንም እንደነበረ ነው፡፡ ስለዚህም የጤና ተቋ ሞች በዚህ ጥናት በመመርኮዝ አስፈላጊውን ድጋፍ ለእናቶች መስጠት ይገባቸዋል፡፡ ለምሳሌም በእርግዝና ጊዜ ብረት ወይንም  Iron  የተባለውን ንጥረ ነገር መስጠት ፣ለወሊድ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ማድረግ፣ በወሊድ ሰአት በጤና ተቋማት በሰለጠነ ባለሙያ እንዲወልዱ ማድረግ ፣ሲወልዱ ደግሞ ማህጸናቸው እንዲኮማተር የሚያግዙ መድሀኒቶችን መስጠት ተገቢ ሲሆን ሕብረተሰቡም እናቶችን እህቶችን ልጆችን እንዲሁም ሚስትን ለማዳን ሲል በፈቃደኝነት ደም መለገስ ይጠበቅበታል፡፡ ንጽህናውን የጠበቀ እና ለእናቶች ክብር የሚሰጥ ጤና ተቋም ሊኖር ይገባል፡፡ ማንኛውም ሰው ደም በመለገስ ምክንያት እናት አተረፈ ማለት ሐገር አተረፈ ማለት መሆኑን ሊረዳ ይገባል፡፡”
ቀደም ሲል የነበሩት የእናቶች ሞት ምክንያቶች ተወግደዋል በሚያሰኝ ሁኔታ ያሉ ሲሆን በአሁን ወቅት አስቸጋሪው እና ለሞት የሚያበቃው የደም መፍሰስ ነው ሲባል ምናልባትም ቀድሞ ተጠቃሽ ከነበሩት እንደ መዘግየት ፣በኢኮኖሚው አለመዘጋጀት፣ የመጉዋጉዋዣ ማጥት ከመሳሰሉት ጋር አሁንም የሚገናኝበት መንገድ አለ ዶ/ር አዝማች ሐዱሽ እንደሚገልጹት፡፡
“...በወሊድ ጊዜ የማህጸን መጥበብ ፣የማህጸን መተርተር ፣ኢንፌክሽን የመሳሰሉት በዋናነት ለእና ቶች ሞት ምክንያት ነበሩ፡፡እነዚህ የሞት መንስኤዎች ከ3-5 ቀን ድረስ እናቶችን አይገድ ሉም፡፡ የደም መፍሰስ ግን በሁለት ሰአታት ውስጥ አንዲትን እናት ለሞት ያበቃል፡፡ ስለዚህም እናቶች በምንም ምክንያት ወደሆስፒታል ለመሄድ መዘግየት የለባቸውም። እናቶች በምንም ምክንያት በቤት ውስጥ መውለድ የለባቸውም፡፡ እናቶች ምንጊዜም በሰለጠነ የሰው ኃይልና በጤና ተቋም መውለድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እናቶች ከጤና ተቋም በእርቀት የሚኖሩ ከሆነም ወደ እናቶች ማቆያ መግባት እና የወሊድ ቀናቶችን መጠበቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡ኢትዮጵያ በ2020/50% የእናቶች ሞት እንቀንሳለን የሚል እቅድ አላት፡፡ስለዚህም 50 % የሚሆኑትን በመድማት ምክንያት የሚሞቱ እናቶች ማትረፍ ከተቻለ በ2020/ ከ50 % በላይ የእናቶችን ሞት መቀነስ ይቻላል፡፡”

Read 2426 times