Print this page
Saturday, 17 March 2012 10:17

“የአንበሳው ታሪክ” የሥዕል አውደርዕይ ዛሬ ይከፈታል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በሰዓሊ ዳዊት ገረሱ የተዘጋጁ 34 የቀለም ቅብና ፎቶግራፍ ሥዕሎች የሚቀርቡበት “የአንበሳው ታሪክ” የተሰኘ የሥዕል አውደርእይ ዛሬ ማታ በታሊስማን የሥዕል አዳራሽ ይቀርባል፡፡ ስለ ስራዎቹ ይዘት ከዝግጅት ክፍላችን የተጠየቀው ሰዓሊው፤ በኢትዮጵያውያን የአንበሳ እሳቤ ላይ ተንተርሶ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል፡፡

ዘመን ባንክና በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ጥናት ማዕከል ስዕሎቹን እንደገዙለት የገለፀው ሰዓሊው፤ ከዚህ ቀደም በገብረክርስቶስ ደስታ ሥነጥበባት ማዕከል ሥራዎቹ እንደታዩለትና የአሁኑ አራተኛው በግል የቀረበ አውደ ርእይ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ የስዕል ተመልካችንና ገበያውን በተመለከተ ሲናገርም፤ “ሕዝቡን ወደ ጥበቡ እንጐትታለን፤ ከአውደርዕዩ ሌላ በተለያዩ መድረኮች እናስተምራለን” ብሏል - ሰዓሊው፡፡

 

 

Read 1410 times Last modified on Saturday, 17 March 2012 10:20