Sunday, 05 February 2017 00:00

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(7 votes)

(ስለ ስደተኞች)

   · ትራምፕ የሽብር ጉዳይ ይሄን ያህል ካሳሰበው፣ ለምንድን ነው ሳኡዲ አረቢያ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳ ከተጣለባቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ ያልተካተተችው?
  ራይሞንድ ስሚዝ (ከአውስትራሊያ)
· ጥገኝነት መጠየቅ ሰብዓዊ መብት ነው፡፡
  አምነስቲ ኢንተርናሽናል
· እዚህ ስደተኞች የሉም፤ የተፈናቀሉ ሰዎችም የሉም፤ … እንግዶቻችን ናቸው፤ እናም የምናስተናግዳቸው በዚያ መልኩ ነው፡፡
  ማይክ ተርነር (በኮንግረስ የኦሃዮ ተወካይ)
· በሶሪያ የቀረን ምንም ነገር የለም፡፡ ውድመት ብቻ፡፡
  ኢብራሂም (የ21 ዓመት ሶርያዊ፤ለCNN የተናገረው)
· እዚህ የሚመጣ ስደተኛ ሁሉ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንግሊዝኛ መማር ወይም አገሪቱን ለቆ መውጣት አለበት፡፡
  ፕሬዚዳንት ቴዎዶር ሩስቬልት
· ስደተኞች ወንጀለኞች አይደሉም፡፡ እዚህ በመኖራቸውና ለኢኮኖሚው አስተዋጽኦ በማድረጋቸው ሊቀጡ አይገባም፡፡
  ሚሼል ሎፔዝ
· ሰዎች ህገ-ወጥ ስደተኞችን ሥራ መቅጠር ማቆም አለባቸው፡፡
  ሂላሪ ክሊንተን
· በአሪዞና ግዛት ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ያላቸው ስደተኞች አለመስፈራቸውን ማረጋገጥ አለብን ብዬ አምናለሁ፡፡
  ዶውግ ዱሴይ (የአሪዞና ገዢ)
· ዛሬ 75 በመቶ የሚሆነው የፍልስጤም ህዝብ ተፈናቅሏል፡፡ በመላው ዓለም 5 ሚሊዮን ፍልስጤማዊ ስደተኞች ይገኛሉ፡፡
  ኢስማይል ሃኒዬህ (የሃማስ ምክትል መሪ)
· ድንበሩን መቆጣጠር የማይችል አገር፣ ከአገር አይቆጠርም፡፡
  ፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬገን
· አውሮፓ የስደተኞችን ጉዳይ ምላሽ መስጠት ከተሳናት፣ የምንመኛትን አውሮፓ አትሆንም።
  አንጄላ መርከል (የጀርመን ቻንስለር)

Read 2564 times