Monday, 30 January 2017 00:00

በአዲስ አበባ የሊንከን ዩኒቨርሲቲ ነገ ተማሪዎችን ያስመርቃል

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(1 Vote)

ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አዲስ አበባ፣ አሜሪካ ከሚገኘው ሊንከን ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለ6ኛ ጊዜ በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን (ኤም ቢ ኤ) እና በመጀመሪያ ዲግሪ (ቢኤ) ፕሮግራም ለመጀመሪያ፣ ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነገ በኢሲኤ አዳራሽ ያስመርቃል፡፡
ዌስተርን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ፣ ከሊንከን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር፣ ላለፉት አምስት ተከታታይ ዙሮች በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን (ኤምቢኤ) 143 ተማሪዎችን በጥራት አስተምሮ ያስመረቀ ሲሆን ነገ ደግሞ 27 ተማሪዎችን በኤምቢ ኤ፣ 18 ተማሪዎችን በቢዝነስ አስተዳደር (ቢኤ) በመጀመሪያ ዲግሪ እንደሚያስመርቅ ታውቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በሚቀጥለው ዓመት በዳይኖስቲክ ኢሜጂንግ በድግሪ መርሃ ግብር ሥልጠና ለመጀመሪያ በዝግጅት ላይ መሆኑን የተቋሙ ፕሬዚዳንት አቶ አቤቱ መላኩ የገለፀ ሲሆን፣ በጥራት ላይ ተመስርቶ ብቃት ያላቸው ዜጎች ኮትኩቶ ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ ከመዋለ ህፃናት ጀምሮ እስከ ድህረ ምረቃ የሚደርስ የትምህርት መርሐ ግብር ለመዘርጋት ማቀዱን ገልጸዋል፡፡

Read 1239 times