Saturday, 17 March 2012 10:04

ማዶና በማላዊ መንግስት ተወቀሰች

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

የፖፕ ሙዚቃ ንግስቷ ማዶና በማላዊ መንግስት ወቀሳ የተሰነዘረባት ሲሆን “እሷ ጭንቀቷ ለአገራችን ለምታደርገው የትምህርት ድጋፍ ሳይሆን ለዓለም አቀፍ ዝናዋ ነው” ተብላለች፡፡ አገራችን በማዶና ሥራ ተሰላችታለች ያሉት የማላዊ የትምህርት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፤  “በመጀመርያ የሴቶች አካዳሚ እገነባለሁ ብላ ነበር፤ ያንን እቅዷን ሰረዘች፤ አሁን ደግሞ በማላዊ 10 ትምህርት ቤቶችን እገነባለሁ በማለት ዘመቻ ጀምራለች፤ ነገር ግን ለእኛ ያሳወቀችው ነገር የለም፤ ፈቃድም አልሰጠናትም” ሲሉ ወቅሰዋታል፡፡ የማዶና ግብረሰናይ ድርጅት በበኩሉ፤ “በምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ወቅታዊ መረጃዎችን ስንሰጥ ቆይተናል፤ የቀረበብን ወቀሳ ከእውነት የራቀ ነው” በማለት አስተባብሏል፡፡

ሁለት ማላዊ ህፃናትን በጉዲፈቻ ወስዳ እያሳደገች የምትገኘው ማዶና፤ በማላዊ የትምህርት ዕድገት ዙርያ የላቀ ሚና መጫወት እንደምትፈልግ በይፋ መናገሯ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ሰሞኑን ከማላዊ መንግስት የተሰነዘረባት ወቀሳ ፍላጐቷ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም ተብሏል፡፡ የ51 ዓመቷ አቀንቃኝ ማዶና፤ ላለፉት አምስት ዓመታት 11ሚ. ዶላር ወጪ በማድረግ 1000 ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ ት/ቤቶች ለመገንባት ስትንቀሳቀስ ቆይታለች፡፡

 

 

Read 1361 times Last modified on Saturday, 17 March 2012 10:06