Saturday, 17 March 2012 10:02

ሜሪል ስትሪፕ ሂላሪን በፊልም እንድትተውን ተጠየቀች

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ሜሪል ስትሪፕ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ሮድሃም ክሊንተንን በፊልም እንድትተውን መጠየቋን “ዋሽንግተን ፖስት” ገለፀ፡፡ “አይረን ሌዲ” በተባለው ፊልም የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጋሬት ታቸርን ወክላ የተወነችው ሜሪል ስትሪፕ፤ ዘንድሮ “ምርጥ ተዋናይት” ተብላ ኦስካር መሸለሟ ይታወሳል፡፡ ሰሞኑን “ዉመን ኢን ዘ ዎርልድ” በተባለ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ በክብር እንግድነት የተሳተፈችው ተዋናይዋ፤ ከሂላሪ ክሊንተን ጋር እንደተገናኘችና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አድናቆት እንዳገኘች ተዘግቧል፡፡

ከ30 ዓመታት በላይ በፊልም ትወና ሙያ ላይ ያሳለፈችው ስትሪፕ፤ ለ17 ጊዜያት በምርጥ ተዋናይነት ለኦስካር ታጭታ፣ ሦስት ጊዜ ሽልማቱን ወስዳለች፡፡ ከ50 በላይ ፊልሞች የሰራችው ሜሪል ስትሪፕ፤ በመላው ዓለም 3.6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝታለች፡፡ ተዋናይቷ በአንድ ፊልሟ በአማካይ 39 ሚሊዮን ዶላር እንደምታስገባ የቦክስ ኦፊስ አሃዛዊ መረጃ ይጠቁማል፡፡

 

 

 

Read 1206 times Last modified on Saturday, 17 March 2012 10:04