Saturday, 17 March 2012 09:57

ኦባማ ለምርጫ ዘመቻ ከሆሊውድ በቂ ድጋፍ አላገኙም

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ከአራት ዓመት በፊት በከፍተኛ ድጋፍ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በመሆን የተመረጡት ባራክ ኦባማ፤ በቀጣዩ ዓመት ህዳር ወር በሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ ለመመረጥ ዘመቻ እያካሄዱ ሲሆን ከሆሊውድ በቂ ድጋፍ እንዳላገኙ “ዘ ሃፊንግተን ፖስት” ዘገበ፡፡ ከአራት አመት በፊት ሆሊውዶች ለኦባማ መመረጥ በቅስቀሳም ሆነ በገንዘብ ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ዘንድሮ ግን ድጋፉ በአንዳንድ ዲሞክራት የሆሊውድ ዝነኞች ብቻ ተወስኗል ብሏል፡፡

ኦባማ ከአራት ዓመት በፊት ለምርጫ ሲወዳደሩ የ9.2 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ከሆሊውድ አግኝተው የነበረ ሲሆን፣ ዘንድሮ ግን 4 ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንዳገኙ ታውቋል፡፡ በዲሞክራት ፓርቲ ደጋፊነታቸው የሚታወቁት የፊልም ባለሙያዎቹ ቶም ሃንክስ፤ ጆርጅ ኩሉኒና አሌክ ባልዲውን ኦባማ በድጋሚ እንዲመረጡ ይፋ ድጋፍ እየሰጡ ከሚገኙት የሆሊውድ ዝነኞች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፡፡

 

Read 1465 times