Saturday, 14 January 2017 16:00

‹‹ህብረ ብዕር 3ኛ ሰኞ ይመረቃል››

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

የአንጋፋው ደራሲና ጋዜጠኛ ካህሳይ ገ/እግዚአብሔር ‹‹ህብረ ብዕር 3ኛ›› የተሰኘ መፅሐፍ ከነገ በስቲያ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር
እንደሚመረቅ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ኤዞፕ ኮሚዩኒኬሽን አስታወቀ፡፡በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነፅሁፍና ፎክሎር ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ፈቃደ አዘዘ ‹‹ስነ ቃል›› በሚል ርዕስ ፅሁፍ የሚያቀርቡ ሲሆን መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ‹‹አዲሱ ትውልድና የአብነት ትምህርት›› በሚል ያቀርባሉ ተብሏል፡፡የስነፅሁፍ መምህሩ የሻው ተሰማ (የኮተቤው) በመፅሀፉ ላይ ዳሰሳ ያደርጋሉ፡፡ ዲያቆን ዳንኤል
ክብረት ‹‹እምነትና ባህል በህብረ ብዕር›› በሚል ርዕስ ፅሁፍ የሚያቀርብ ሲሆን ጋዜጠኛ ንጉሴ ተሰማ ስለደራሲው ገለፃ እንደሚያደርጉ ታውቋል።

Read 893 times