Saturday, 31 December 2016 11:13

ዶ/ር መረራ ጉዲና የ28 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው

Written by  ማህሌት ፋሲል
Rate this item
(11 votes)

ከትናንት በስቲያ በአራዳ መጀመሪያ ደረጃ ምድብ ችሎት የቀረቡት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ ፖሊስ፤ የ28 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የጠየቀባቸው ሲሆን ፍ/ቤት ጥያቄውን ተቀብሎ ለጥር 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፖሊስ ባለፈው በጠየቀው የ28 ቀን ቀጠሮ፤ ቅድመ ምርመራ ማድረጉን ጠቁሞ ከፌስቡክና ከኢ-ሜል ያገኛቸውን ፅሁፎች ትርጉም ቤት ልኮ ለማስተርጎምና ለተጨማሪ ምርመራ ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁን አመልክቷል፡፡
ዶ/ር መረራ ለፍ/ቤቱ ሲያስረዱ “ሽብርተኝነት መጥፎ እንደሆነ ሳስተምር ኖሬአለሁ፤ ዘመኔን ሁሉ በሰላማዊ መንገድ ነው ስታገል የቆየሁት” ብለዋል፡፡
ጠበቆች ዋስትና ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ዶ/ር መረራ በሽብር የተጠረጠሩ በመሆኑ ዋስትና እንደማያሰጣቸው ፍ/ቤቱ አመልክቶ እስከ ቀጣይ ቀጠሮ በማረሚያ ቤት ቆይተው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ በይኗል፡፡
ዶ/ር መረራ ባለፈው ህዳር 21 በአውሮፓ ቆይታቸው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ፣ ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት ፈጥረዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል፡፡ 

Read 4469 times