Saturday, 17 December 2016 12:52

የጡት ወተት በሽታን የመከላከል አቅም አለው

Written by 
Rate this item
(3 votes)

 ሕጻናት ከተወለዱ ከስድስት ወር በሁዋላ ተጨማሪ ምግብ እያገኙ እስከ ሁለት አመት እድሜአቸው ድረስ የጡት ወተት መመገብ ሊቋረጥባቸው አይገባም።
 ሕጻናት ሁሉ በትክክል ጡት ወተት ከተመገቡ በየአመቱ በአለም እስከ 800,000 ልጆችን ሕይወት ማዳን ይቻላል።
 በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚወለዱት ሕጻናት ከ40% በታች የሆኑት ሙሉ በሙሉ የጡት ወተት አግኝተዋል ማለት ይቻላል።
 WHO-
       
 ሕጻናት ከተወለዱ ከስድስት ወር በሁዋላ ተጨማሪ ምግብ እያገኙ እስከ ሁለት አመት እድሜአቸው ድረስ የጡት ወተት መመገብ ሊቋረጥባቸው አይገባም።
ሕጻናት ሁሉ በትክክል ጡት ወተት ከተመገቡ በየአመቱ በአለም እስከ 800,000 ልጆችን ሕይወት ማዳን ይቻላል።
በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚወለዱት ሕጻናት ከ40% በታች የሆኑት ሙሉ በሙሉ የጡት ወተት አግኝተዋል ማለት ይቻላል።
 WHO-
    ጡት ማጥባት ከምንም በላይ ለልጆች ጠቃሚ ነው ቢባልም አንዳንድ ጊዜ ግን ልጆች የሚጎዱበት ምክንያት እንደሚያጋጥም ግልጽ ነው። ይኼውም ከጤና አኩዋያ ሲሆን ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው።
ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ ከሚተላለፍባቸው መንገዶች አንዱ ጡት የማጥባት ወቅት ነው። ሌላው ሕመም ደግሞ የሳንባ በሽታ ሲሆን በተለይም በወቅቱ ካልታከመ ይህ ለሕጻኑ ጉዳት ለስከትል ይችላል። የካንሰር ሕመም ገጥሞአት ኬሞራፒ የተባለውን ሕክምና የምትከታተል እናት ልጁዋን ጡት በምታጠባበት ወቅት ለልጁዋ ሕመምን ሊያስከትል ይችላል።
ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ እንደ ኮኬይን ፣ማሪዋና፣ሲጋራ ማጨስና መጠጥ አዘውትራ የምት ጠጣ እናት ልጁዋን በምታጠባበት ወቅት ለልጁ ጎጂ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ መድሀኒቶችን ለምሳሌም ማይግሪን ለተሰኘው ከባድ የራስ ሕመም እና ተመሳሳይ የጤና ችግሮች በሐኪም ትእዛዝ የሚወሰዱ መድሀኒቶችም የጡት ወተቱን ጎጂ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ስለዚህ ምንም አይነት የጤና እና የባህርይ ችግር ቢኖር ጡት ለማጥባት መቻል አለመቻልን ከሕክምና ባለሙያ ጋር መምከር ጠቃሚ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ጎጂ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ እንደ ጉንፋን ወይም የብርድ ሕመም የመሳሰሉት ጡት ከማጥባት የሚያግዱ አይደሉም። የጡት ወተት በእራሱ በሽታን የመከላከል አቅም ስላለው ጡት የሚጠባውን ልጅ ከሕመም ሊከላከልለት ይችላል። አንዳንድ የህክምና ጠበብት ሕጻን ከተወለደ ከ4/ወር ጀምሮ አይረንና ቫይታሚን ዲ የተሰኙትን ንጥረነገሮች በሐኪም ትእዛዝ መስጠት ይችላል። ነገር ግን ለሕጻኑም ሆነ ለእናትየው ይህ ድጋፍ ሰጪ ቋበቅቅቁስቂስቃቋ ከመቼ ጀምሮ እና ምን ያህል መወሰድ እንዳለበት ሐኪምን ማነጋገር ያስፈልጋል።
እናቶች ልጆቻቸውን ለምን ጡት ማጥባት አይፈልጉም?
አንዳንድ እናቶች ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ልጆቻቸውን ሲያጠቡ መታየት አይፈልጉም። ምናልባትም የሁዋላቀርነት ምልክት አድርገው ሊወስዱት ይችላሉ።አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የልጁ አባት ወይንም በቤት ውስጥ ልጁን የሚንከባከቡ ቤተሰቦች ጡጦ በማዘጋጀት ሊሰጡት ስለሚ ችሉ ልጁ ተጎጂ አይደለም...እንዲያውም ተጠቃሚ ነው ብለው የሚያስቡ ይኖራሉ። ከዚህ በተጨማሪም ልጆች ከጡት ወተት ይልቅ የተዘጋጀ ወተትን በቀስታ ይመገባሉ። የጡት ወተት ግን በተደጋጋሚ ሊወስዱት የሚችሉት ቀለል ያለ ምግብ ስለሆነ ምናልባትም የሚጠግቡት በተዘጋጀው ወተት ስለሆነ በእርጋታ ይመገባሉ የሚል እሳቤ የሚኖራቸው እናቶች ይኖራሉ።ይህ ግን ተክክል ስላልሆነ የወለዱትን ልጅ ጡት በተገቢው መንገድ ማትባት ጠቃሚነት አለው።
ጡት ለማጥባት አስቸጋሪ ሁኔታዎች
የጡት ጫፍ መቁሰል
ልጅ እንደተወለደ በመጀመሪያው ሳምንት የጡት ጫፍ መቁሰል እንደሚኖር አስቀድሞ ማወቅ ብልህነት ነው። ልጁ በትክክል ጡት መያዙን ማረጋገጥ እና ሲጨርስም ጡቱን ከአፉ ከመጎተት ይልቅ አንድ ጣትን ወደልጁ አፍ በመክተት ጡቱን ከአፉ ለማውጣት በቂ ክፍተት መፍጠር ይጠቅማል።ቁስለቱ ቶሎ የማይድን ከሆነ ጡት ባጠቡ ቁጥር ወተቱን ጨርሶ እንዲጠባ እና ጡቱ እንዳያግት ማድረግ ይጠቅማል። ይህ ካልሆነ ግን ጡቱ በወተት ይሞላል ፣ያብጣል ፣ ሰለሆነም ሕመም ይኖረዋል። ልጅ ከጠባ በሁዋላ ድጋሚ እስኪሰጠው ባለው ጊዜ ጡቱ ደረቅ እንዲሆን ማድረግ ይጠቅማል። ልጁ ደጋግሞ በጠባ ቁጥር በጡት ጫፍ ላይ ያለው ቁስለት እየቀነሰ እንዲያውም እየዳነ ይሄዳል። ስለዚህ የጡት ጫፍ ቆሰለ ተብሎ ልጁ ጡት ከመጥባት መታገድ የለበትም።
ደረቅና የተሰነጣጠቀ የጡት ጫፍ
የጡት ጫፍን ለማጽዳት የሚጠቀሙበት ሳሙና ወይንም የሽቶ መአዛ ያላቸው ቅባቶች እና ሎሽኖች በውስጣቸው አልኮል ስላላቸው ማስወገድ ተገቢ ነው። ከጡት ማጥባት በሁዋላ ንጹህ የሆኑ ጠረን የሌላቸው ቅባቶችን መጠቀም ይጠቅማል። ቅባት ከተቀቡ በሁዋላ ጡት መልሶ ለማጥባት የተቀባውን ቅባት በደንብ ማጠብና ማስወገድ ያስፈልጋል። የጡት መያዣዎ ከጥጥ የተሰራ እንዲሆን ይመከራል።
በቂ የጡት ወተት የለኝም ብሎ መጨነቅ
አንድ ልጅ በቀን በበቂ ሁኔታ ጡት ጠብቶአል ወይንም ተመግቦአል የሚባለው በቀን ከ6 እስከ 8 ዲያፐር ሲቀይር ነው። አንድ ልጅ እስከ 6 ወር ድረስ ካለምንም ተጨመቀሪ ምግብ የጡት ወተት መጥባት አለበት። የእናትየው ሰውነት የልጁን ጡት መጥባት ፍላጎት በየተወሰነው ሰአት ስለሚረዳ ማለትም ጡቱ ወተት ስለሚሞላ ቸል ባለማለት በተገቢው ማጥባት ይገባል። ጡት በተሳበ ቁጥር ወተቱም መመረቱ ይቀጥላል። አንዳንድ ሴቶች ጡታ ቸው በተፈጥሮው ትንሽ ስለሆነ ወተት የለኝም ብለው ያስባሉ። ነገር ግን የጡት መጠን መተ ለቅ ወይንም ማነስ ወተትን በማምረት በኩል ምንም ልዩነት የለውም። እናቶች ባቅማቸው ጥሩ መመገብ ፣ተገቢ የሆነ እረፍት ማድረግ እና ጡታቸውን በተገቢው እያጸዱ ማድረቅ ልጃቸውን ለማጥባት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል።
ጡትን ማለብና ወተቱን ማስቀመጥ
ጡቱን በእጅ በመጭመቅ ወይንም በማለቢያ በማለብ የጡት ወተት እንዲገኝ ያስችላል። በተ ለይም እናቶች በቶሎ ወደስራ የሚሄዱ ከሆነ የታለበ የጡት ወተት ማግኘት ስላለባቸው በእቃ መመገቡን አስቀድሞ ማለማመድ ያስፈልጋል። የጡት ወተት ከታለበ በሁዋላ እስከሁለት ቀን ድረስ በማቀዝቀዣ ውስጥ በማስቀመጥ መጠቀም ይችላል። የቀዘቀዘውን የጡት ወተት በማይ ክሮዌቭ ማሞቅ ግን ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ሊያሳጣ ስለሚችል አይመከርም። የታለበውን የጡት ወተት ለልጁ መስጠት ሲያስፈለግ ከማቀዘቀዣ ውስጥ በማውጣት ትንሽ ማቆየት ወይ ንም የሞቀ ውሀ በሳህን ውስጥ አድርጎ ወተቱን የያዘውን እቃ በሳህኑ ውስጥ ማስቀመጥ ያስፈልጋል።
ጡት በወተት መሞላት
ጡት በወተት ሊሞላ ወይንም ሊወጠር ይችላል። ጡቱ በወተት መሞላቱ ትክክለኛና ተፈጥሮ አዊ ነው። ነገር ግን በጡት ላይ ያሉት የደም ስሮች ሊወጣጠሩና ሊጨናነቁ ይችላሉ።በዚህ ጊዜ ጡት ጠጣር ይሆናል። እንዲሁም በመወጣጠሩ ሕመም ይሰማል። በዚህ ጊዜ በበረዶ በቀዝቃ ዛው ወይንም ሙቅ ሻወር በመውሰድ እንዲላላ ማድረግ ይቻላል።
የጡት ወተት የሚፈስበት መስመሮች
መጠጠር ወይም መታመም
በጡት ውጫዊ አካል ላይ የሚታዩ ቀያይ ወይንም ትኩሳት ያላቸው ነጠብጣቦች የጡት ወተት መፍሰሻው መታመሙን ሊያመላክቱ ይችላሉ። ይህንን አካባቢ በጥንቃቄ መዳሰስ ወይንም ሙቀት እንዲሰማ ጨመቅ ጨመቅ በማድረግ እንዲላላ እና እንዲፍታታ በማድረግ የጠጠረ ውን ነገር እንዲወገድ ማድረግ ይቻላል።
የጡት ኢንፌክሽን
የጡት ኢንፌክሽን ወይንም መመረዝ የሚገጥመው የተሰነጣጠቀው ጡት ከልጁ አፍ ከወጣ በሁዋላ በባክሪያ ሲያዝ ነው።ጡት የመመረዝ ባህርይ ሲያሳይ ትኩሳትና መሰል ስሜቶች ከተስተዋሉ ሐኪምን ማማከር ያስፈልጋል።
ጭንቀት
አንዲት እናት ጭንቀት ካለባት የጡት ወተትዋ ፍሰቱን ሊቀንስ ይችላል። ሰውነት በተፈጥሮው ያመረተውን ወተት ጭንቀት ቢያግደውም ልጁ መጥባት ሲፈልግና እናትየው የልጅዋን ጡት መፈለግ ስታይ ግን ከጭንቀት ስለምትላቀቅ ያን ጊዜ ወተት እንደልብ መፍሰስ ይጀምራል። ስለዚህ የምታጠባ እናት በተቻለ መጠን ዘና ማለት እና መደሰት እንጂ መጨነቅ የለባትም።
እድገቱ ያልተሟላ ሕጻን
አንድ ሕጻን ካለቀኑ ከተወለደና አቅም ከሌለው ጡት መሳብ ሊያቅተው ይችላል። በዚህ ጊዜ የጡት ወተቱን በማለብ በጡጦ ለልጁ ማጠጣት ይገባል።
ባጠቃላይም የተወለደ ልጅን የጡት ወተት መመገብ ተፈጥሮአዊና ጤናማ ተግባር ነው። ነገር ግን ከሐኪም ጋር መመካከር የሚያስፈልግበት አጋጣሚ እንደሚኖር መዘንጋት የለበትም።
ጡት ባልተለመደ ሁኔታ የመቅላት የመቁሰል የመጠንከር እና የመሳሰሉትን ምልክት ካሳየ
ከጡት ውስጥ በጫፉ በኩል ፈሳሽ ወይንም ደም የሚወጣ ከሆነ
ሕጻኑ ክብደቱ እየቀነሰ የሚሄድ ከሆነ ሳይውሉ ሳይድሩ ከሐኪም ጋር መመካከር ያስፈልጋል።  
ምንጭ፡- WebMD, LLC

Read 6676 times