Print this page
Monday, 05 December 2016 08:58

የፀሐፍት ጥግ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

   (ስለ ንባብ)
ጥቂት ገንዘብ ሳገኝ መፃህፍት እገዛለሁ፡፡ ከተረፈኝ ምግብና ልብሶች እገዛለሁ፡፡
ኢራስመስ  
መፅሃፍ በእጃችሁ የያዛችሁት ህልም ነው፡፡
ኔይል ጌይማን  
ከፀሃፊው ጋር ለግማሽ ሰዓት የማውራት ዕድል ባገኝ፣ መፅሃፉን ጨርሶ አላነብም ነበር።
ውድሮው ዊልሰን  
ህይወትን እንደ ጥሩ መፅሃፍ ነው የማስበው። የበለጠ ዘልቃችሁ በገባችሁ ቁጥር የበለጠ ትርጉም መስጠት ይጀምራል፡፡
ሃሮልድ ኩሽነር
ሁሉም ሰው የሚያነበውን መፃህፍት ብቻ የምታነቡ ከሆነ፣ ሁሉም ሰው የሚያስበውን ብቻ ነው የምታስቡት፡፡
ሃሩኪ ሙራካሚ
ጥሩ ልብወለድ ስለጀግና ገፀ ባህሪው እውነታው ይነግረናል፤ መጥፎ ልብወለድ ግን ስለደራሲው እውነታውን ይነግረናል፡፡
ጊልበርት ኬ.ቼስተርን
መፅሃፍ ማንበብ ለራስህ ደግመህ እንደመፃፍ ነው።
አንጌላ ካርተር
አንባቢዎችን በሁለት መደቦች እከፍላቸዋለሁ፡- ለማስታወስ የሚያነቡና ለመርሳት የሚያነቡ፡፡
ዊሊያም ሊዮን ፌልኝስ
የማታውቀው ነገር ታላቅ መፅሃፍ ይወጣዋል።
ሲድኒ ስሚዝ
መፃህፍትን ከማቃጠል የከፉ ወንጀሎች አሉ። ከእነሱም አንዱ አለማንበብ ነው፡፡
ጆሴፍ ብሮድስኪ
ዙሪያዬን በመፃህፍት ካልተከበብኩ በቀር እንቅልፍ አልተኛም፡፡
ጆርጅ ሉዊስ ቦርጌስ
መፅሃፍ ምናብን የማቀጣጠያ መሳሪያ ነው፡፡
አላን ቤኔት
ጥሩ መፅሃፍ መጨረሻ የለውም፡፡
አር.ዲ.ኩሚንግ

Read 3295 times
Administrator

Latest from Administrator