Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 March 2012 12:00

የኪነጥበባት በጎ አድራጎት ማህበር ከልዑል አስፋወሠን ጋር ተወያየ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

እርዳታ ከውጭ ለማሰባሰብ ቃል ገብተዋል

አምና በበጎ አድራጎት ድርጅትነት የተቋቋመው የኢትዮጵያ የኪነ-ጠቢባን ማህበር በአርቲስቶች አጠቃላይ ችግሮች ዙሪያ ከዶ/ር ልኡል አስፋወሠን ጋር የተወያየ ሲሆን ነዋሪነታቸውን በጀርመን ያደረጉት ልዑሉ፤ በዚያ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንና ሌሎች ለጋሾችን በማስተባበር እርዳታ ለማሰባሰብ ለማህበሩ ቃል ገቡ፡፡ ቅዳሜ ረፋድ ላይ ካዛንቺስ በሚገኘው አዲሱ ራዲሰን ብሉ ሆቴል በተካሄደው ስብሰባ፣ ልዑሉ 200 መፃሕፍትና ለስኳር ሕመምተኞች የሚሆኑ 200 ጃኬቶችን ለማህበሩ አበርክተዋል፡፡

“ለከያንያን እንኳን የመኖሪያ የመቃብር ሥፍራ ማግኘት አስቸጋሪ እንደሆነ በአስናቀች ወርቁ አየሁ” ያሉት የማህበሩ ፕሬዚዳንት ገጣሚና ፀሃፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፤ “አርቲስቱ ለምን የራሱ መቀበርያ አይኖረውም” ሲሉ ጠይቀዋል - በዕለቱ ባደረጉት ንግግር፡፡ አንጋፋው የማስታወቂያ ባለሙያ አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ ደግሞ፤ የገንዘብ አቅም ያላቸው ወገኖች የበጎ አድራጎት ድርጅቱን እንዲደግፉ እጥራለሁ ካሉ ነኋላ ተለማኙ ለማኝ መሆኑ ያሳዝናል፡፡” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡

 

ልዑል አስፋወሠን አስራተ ካሳ በበኩላቸው፤ “የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ መቃብር ወድቆ ሳይ ነው የዚህ ማህበር አባል ለመሆን ቃል የገባሁት” ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያየ የኪነጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ 10ሺህ ባለሙያዎች እንደሚገኙ ከማህበሩ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፤የኪነጥበባት በጎ አድራጎት ማህበሩ በተቋቋመበት ወቅት የኤፌዲሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስን የበላይ ጠባቂው ማድረጉ ይታወሳል፡፡

 

 

Read 2508 times Last modified on Saturday, 10 March 2012 12:04