የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያዘጋጀውን ሁለተኛውን የባህል አውደርዕይ ባለፈው ሳምንት ከማክሰኞ እስከ ሐሙስ አቀረበ፡፡ አራት ኪሎ ምኒሊክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ሜዳ ላይ ለሦስት ቀን በተካሄደው አውደርእይ ከአዲስ አበባ እና ከሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተለያዩ በእጅ የተሰሩ ቅርፃቅርፆች፣ የቆዳና የጨርቅ አልባሳት እና ሌሎች የየብሄረሰቡ መገለጫ ቁሳቁሶች ለእይታና ለገበያ ቀርበዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዘክር አዳራሽ ውስጥ ሰሞኑን በእደጥበብ ሥራዎች ዙሪያ አውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡
Saturday, 10 March 2012 11:57
ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሁለተኛውን የባህል ባዛር አቀረበ
Written by መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና