Print this page
Saturday, 10 March 2012 11:57

ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ 7ኛ መፅሐፉን ለንባብ አበቃ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(8 votes)

የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር ዋና ፀሐፊ የሆነው ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ሰባተኛ መፅሐፉን “ጽላሎት” በሚል ርዕስ ባለፈው ረቡዕ ለንባብ አበቃ፡፡ 11 ታሪኮችን የያዘው የአጫጭር ታሪኮች መድበል በ30 ብር እየተሸጠ ነው፡፡በቅርቡ የማስተርስ ዲግሪውን በፎክሎር የትምህረት ዘርፍ ያገኘው እንዳለጌታ ከበደ፤ ከአሁን ቀደም “ዛጎል”፣ “ደርሶ መልስ”፣ “ከጥቁር ሰማይ ሥር”፣ “የመኝታ ቤት ምስጢሮች”፣ “ኬርሻዶ” እና “ልብ ሲበርደው” የተሰኙ መፃሕፍትን ለንባብ ያበቃ ሲሆን በሌሎች መድበሎችም ሥራዎቹ ታትመውለታል፡፡

በሌላ በኩል “ሸራፋዶን” የተሰኘ ኢትዮጵያዊ ክዋኔዎችና እንቆቅልሾችን የያዘ የልጆች መጽሐፍ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት በፑሽኪን አዳራሽ ይመረቃል፡፡ መጽሐፉን ያዘጋጀው ብርሃነ ዓለሙ ገሣ ነው፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ በታሪክ መሰለ አበጋዝ የተዘጋጀው “የቀደመው ስህተት እና ሌሎችም” የአጫጭር ልቦለዶች መድብል ትናንት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ተመረቀ፡፡ ዘንድሮ ለንባብ የበቃው፡፡ መጽሐፉ አምስት ታሪኮችን ይዟል፡፡

 

Read 4738 times