Print this page
Saturday, 10 March 2012 11:54

የራስ ተፈሪያን አውደርዕይ ሐሙስ ይከፈታል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

“ስደት፣ ታሪክ፣ ባህልና ሙዚቃ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የራስ ተፈሪያን አውደርዕይ የፊታችን ሐሙስ ማምሻውን በ11፡30 በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴ ይከፈታል፡፡ ሥዕል፣ ፎቶግራፍ፣ ፊልምና ሙዚቃ ያካተተው የሦስት ቀናት አውደርዕይ፤ ትምህርታዊ ገለፃዎችንና ውይይቶችንም ያካተተ ነው፡፡ በአውደርእዩ የተካተቱት ፎቶግራፎች ራስተፈሪያኖቹ ቅድስት ስፍራ በሚሏት የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የትውልድ ቦታ ኤጀርሳ ጎሮ የተነሱ መሆናቸው ሲታወቅ፤ «በአፍሪካ አሜሪካውያን ህይወት የኢትዮጵያ ሚና” በሚል ርዕስ ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ ትምህርታዊ ገለፃ የሰጣሉ ተብሏል፡፡

ባለፈው ረቡዕ ጧት በአሊያንስ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት የአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴ አዲሱ ዳይሬክተር ኦሊቨር ዴንታዥ፤ ይህን ሁለተኛውን አውደርእይ ሕዝቡ በነፃ መከታተል ይችላል ብለዋል፡፡

በአውደርእዮ ላይ የራስ ኃይሉ የሙዝ ጥበብ ሥዕሎች የተካተቱ ሲሆን “ማርከስ ጋርቬ፡- አንጋፋ የጥቁር ፖለቲከኛ” የሚል ፊልምም ይቀርባል፡፡

የሦስቱን ቀን አውደርእይ አሊያንስን ጨምሮ የጀርመን የባህል ተቋም፣ የፈረንሳይ ኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል፣ የዌስት ኢንዲስ ዩኒቨርሲቲ የልማት መካነጥናትና የጐተ ተቋም በጋራ አሰናድተውታል፡፡

 

 

Read 1415 times Last modified on Saturday, 10 March 2012 11:56