Saturday, 10 March 2012 11:52

“የሺዎች እናት” አውደርእይ ተከፈተ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

የአበበች ጐበና የኑዛዜ ሰነድም ቀርቧል

የክብርት ዶ/ር አበበች ጐበና የበጎ አድራጎት ተግባር ላይ ያተኮረው “የሺዎች እናት” የሥዕል፣ የፎቶግራፍ እና የቅርፃቅርጽ አውደርእይ ባለፈው ረቡዕ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዘክር ተከፈተ፡፡ ከትናንት ወዲያ ጀምሮ ለተመልካች ክፍት በሆነው አውደርእይ ላይ በጐ አድራጊዋ ከተለያዩ ሀገር አቀፍ እና ዓለምአቀፍ ተቋማት ያገኟቸው ሽልማቶችና በ1999 ዓ.ም ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለሰብአዊ የበጎ አድራጎት ተግባራቸው የሰጣቸው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለእይታ ቀርበዋል፡፡ ክብርት ዶ/ር አበበች ሰኔ 16/2002 ዓ.ም በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን ዋቢነት በተፈረመ ኑዛዜአቸው፣ ወራሻቸው አበበች ጐበና ህፃናት ክብካቤና ልማት ማህበር መሆኑን፣ ሲሞቱ ሳጥን ሳይገዛ በጨርቅና ሰሌን መቀበር እንደሚፈልጉ፣ ሀዘንተኞች ጥቁር እንዳይለብሱና ሃውልት እንዳይሰራ መፈለጋቸውን የገለፁበት ሰነድም ለእይታ በቅቷል፡፡

 

 

Read 1160 times Last modified on Saturday, 10 March 2012 11:56