Saturday, 10 March 2012 11:35

ክሪስ እና ሪሃና “ፍቅር እንደገና” ብለዋል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(4 votes)

ክሪስ ብራውን እና ሪሃና ለሦስት ዓመት ተራርቀው ከቆዩ በኋላ የፍቅር ግንኙነታቸውን እንደአደሱ ተገለፀ፡፡

ከፍቅር ግንኙነቱ መታደስ ጋር በተገናኘ ሁለቱ በጋራ የሰሯቸው ሁለት ነጠላ ዜማዎች ተፈላጊነቷቸው እንደጨመረ ታውቋል፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት ክሪስ ብራውን በፍቅረኛው በሪሃና ላይ ድብደባ እንደፈፀመባት የሚታወስ ሲሆን ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ ለአምስት ዓመታት አጠገቧ ድርሽ እንዳይል ተከልክሎ ነበር፡፡ ክሪስ ብራውንና  ሪሃና “ፍቅር እንደገና” በማለት ግንኙነታቸውን ዳግም ያደሱ ሲሆን ሁለቱ አቀንቃኞች አዳዲስ  ዜማዎችን በትዊተር ገፆቻቸው ላይ ለቀዋል፡፡ “በርዝ ዴይ ኬክ” በተባለው የሪሃና ሪሚክስ ሙዚቃ ላይ ክሪስ ብራውን ያጀባት ሲሆን “ተርን አፕ ዘ ሚውዚክ” በተባለው የክሪስ ዘፈን ላይ ደግሞ ሪሃና አጅባዋለች፡፡ በሁለቱም የዘፈን ግጥሞች የተንፀባረቁት ሃሳቦች ሁለቱ ዝነኞች ዳግም ፍቅራቸውን ለማሟሟቅ ፍላጎት እንዳላቸው ያመለክታሉ ተብሏል፡፡

 

 

Read 4206 times Last modified on Saturday, 10 March 2012 11:38