Saturday, 10 March 2012 11:21

“ዘ ሎራክስ” የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ቢባልም በገቢ አልተቻለም

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

በታዋቂ የህፃናት መፅሃፍ ላይ ተመስርቶ የተሰራው “ዘ ሎራክስ” የተሰኘው አኒሜሽን ፊልም በአካባቢ ጥበቃ ፕሮፓጋንዳ የታጀበ ነው በሚል ተተቸ፡፡ ባለፈው ሳምንት በሰሜን አሜሪካ  ሲኒማ ቤቶች ለእይታ የበቃው ፊልሙ፤ 70.7 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት የዘንድሮን ከፍተኛ ሳምንታዊ ገቢ አስመዘግቧል፡፡ ፊልሙ ከገቢው 50 በመቶውን ያገኘው በ3ዲ ለእይታ በበቃባቸው ሲኒማ ቤቶች  እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በ1977 እ.ኤ.አ የታተመው “ዘ ሎራክስ” የተሰኘው መፅሃፍ 200 ሚሊዮን ቅጂዎች የተቸበቸበ ሲሆን ዋና ጭብጡ በአካባቢ ጥበቃ ተሟጋችነት ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ መፅሃፉ ለህትመት ከበቃ ከ35 ዓመት በኋላ ታሪኩን በአኒሜሽን ፊልም ያሰራው ዩኒቫርሳል ፒክቸርስ ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር በመቀናጀት ነው፡፡ ፊልሙን በድምፅ ከተወኑት መካከል ዳኒ ዲቬቶ፤ ዛክ ኤፍሮን፤ ቴይለር ስዊፍትና ቤቲ ዋይት ይገኙበታል፡፡

 

 

Read 1398 times Last modified on Saturday, 10 March 2012 11:32