ሐዘኔ
ሌት ቀኑን ሲወርሰው .. ዠንበሯ ስትሞት፤
ብርሃንና ጸዳል … ቀለምና ውበት፤
ተፋዘው ሳያቸው
በጨለማው ዳፍንት …
ባር ባር ይላል ሆዴ … ያዝናል የኔ ስሜት …
ግና ከዚህ በላይ … ግናም ከዚህ በላይ
ነፍሴን የሚጨንቃት … ልቤ ሚሸበረው፤
ቀኑ ሲጨላልም፤ ንጋት እንደሌለው፤
ጥቁር ከል ደርቦ
ልክ እንደ ጨለማው … ይሄን ቀን ሳየው ነው …
ቀኑ በጨለመ … የማይነጋ መስሎት
ነገም ሌላ ቀን ነው ለተሳነው … ማለት
ተስፋው ለሞተበት፡፡
ታደሠ ለገሠ (ሐዋሳ)
ሐዘኔ
ሌት ቀኑን ሲወርሰው .. ዠንበሯ ስትሞት፤
ብርሃንና ጸዳል … ቀለምና ውበት፤
ተፋዘው ሳያቸው
በጨለማው ዳፍንት …
ባር ባር ይላል ሆዴ … ያዝናል የኔ ስሜት …
ግና ከዚህ በላይ … ግናም ከዚህ በላይ
ነፍሴን የሚጨንቃት … ልቤ ሚሸበረው፤
ቀኑ ሲጨላልም፤ ንጋት እንደሌለው፤
ጥቁር ከል ደርቦ
ልክ እንደ ጨለማው … ይሄን ቀን ሳየው ነው …
ቀኑ በጨለመ … የማይነጋ መስሎት
ነገም ሌላ ቀን ነው ለተሳነው … ማለት
ተስፋው ለሞተበት፡፡
ታደሠ ለገሠ (ሐዋሳ)