Sunday, 16 October 2016 00:00

ነገ የኢ/ር ኃይሉ ሻወል መታሰቢያ ይደረጋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

    የቀብር ስነ ስርአታቸው ባለፈው ማክሰኞ በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለተፈፀመው አንጋፋው ፖለቲከኛ ኢ/ር ኃይሉ ሻወል በመኢአድ ፅ/ቤት በነገው እለት የመታሰቢያ ዝግጅት ይደረጋል። በመታሰቢያ ዝግጅቱ ላይ የፓርቲ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ ፖለቲከኞችን ጨምሮ የስራ አጋሮቻቸውና ቤተሰቦቻቸው እንደሚገኙ ከመኢአድ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። ነገ እሁድ ከ8 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው የመታሰቢያ ስነ ስርአት ላይ ኢ/ር ኃይሉ ሻወል፤ በተለይ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ባበረከቱት አስተዋፅኦ ላይ ሶስት ምሁራን ፅሁፍ አቅርበው ውይይት ይደረጋል ብለዋል፤ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ አደና ጥላሁን፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ የስነ ፅሁፍ ፕሮግራሞችም እንደሚካተቱና ከ200 በላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

Read 1317 times