Sunday, 09 October 2016 00:00

የጀርመን መራሄ መንግስት ማክሰኞ አዲስ አበባ ይገባሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

     የጀርመን መራሄ መንግስት አንጌላ መርኬል ማክሰኞ አዲስ አበባን እንደሚጎበኙና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ከስደት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የፊታችን ዘግቧል፡፡
ከሶስት የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር በስደትና ሽብርተኝነትን በመታገል ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን ለማድረግ ያቀዱት መርኬል፤ ነገ ወደ ማሊ እንደሚያቀኑና ከዚያም በኒጀርና በኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን እንደሚቀጥሉ የጠቆመው ዘገባው፤ በአዲስ አበባ ቆይታቸው የአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤትን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አንጌላ መርኬል በአፍሪካ አገራት ለቀናት የዘለቀ ጉብኝት ሲያደርጉ ከአምስት አመታት ወዲህ የአሁኑ የመጀመሪያው እንደሚሆን ዘገባው ጠቁሟል፡፡

Read 3623 times