Monday, 26 September 2016 00:00

የኢሬቻ በአል ከፖለቲካ ነፃ እንዲሆን ኦፌኮ አሳሰበ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(14 votes)

የኩሽ ህዝቦች በተለይም አሮሞዎች ፈጣሪያቸውን በሚያመሠግኑበት ሃይማኖታዊና ባህላዊ የኢሬቻ ስነስርአት ላይ ማናቸውም የፖለቲካ ሃይሎች ከዋዜማው ጀምሮ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ የኦሮም ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አሣሠበ፡፡
መስከረም 22 የሚከበረው የኢሬቻ በአል የራሱ ሃይማኖታዊ ባህልና የአከባበር ስርአት እንዳለው በመግለጫው የጠቀሰው ኦፌኮ፤ የተለያዩ አካላት በዋዜማው ‹‹የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ›› እና ሌሎች ከባህሉ ጋር የማይገናኙ ፕሮግራሞችን ለማካሄድ ማቀዳቸው ተቀባይነት የለውም ብሏል፡፡
በአሉ የምስጋና ቀን በመሆኑ በመልከ መውረጃ መንገዶች ላይ የኪነት ቡድን አደራጅቶ ማስጨፈር፣ የፖለቲካ ንግግር ማድረግ የመሣሰሉትን ፓርቲው እንደሚቃወም አስታውቋል፡፡ በአሉ ከፖለቲካም ሆነ ባህሉን ከሚፃረር ማንኛውም ድርጊት ነፃ እንዲሆንና የህዝብ በአልነቱ እንዲከበር አሳስቧል ኦፌኮ፡፡

Read 3628 times