Monday, 26 September 2016 00:00

ወጋገን ኮሌጅ ዛሬ ተማሪዎቹን ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(6 votes)

ወጋገን ኮሌጅ ላለፉት ሁለት ዓመታት በአካውንቲንግ፣ በፊልምና በቴአትር ጥበባት ያሰለጠናቸውን 120 ተማሪዎች ዛሬ ቦሌ አሮሚያ ታወር ላይ በሚገኘው ሰራዊት ሲኒማ አዳራሽ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ያስመርቃል፡፡ ኮሌጁ ከተቋቋመበት ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ሲያሰለጥን የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ የሚያስመርቅ መሆኑን የኮሌጁ ሬጅስትራር ኦፊሰር ወ/ሪት ሀመልማል በላይ አሞኘ ለአዲ አድማስ ገልፀዋል፡፡ ወጋገን ኮሌጅ በ2008 የበጀት ዓመት የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ 66 ያህል የግል ኮሌጆች መካከል የሰልጣኞቹን የብቃት መረጋገጫ ውጤት 81 በመቶ በማምጣት ለ2009 ዓ.ም የእውቅና ፈቃዳቸውን ካደሱ 12 ኮሌጆች የመጀመሪያው ሆኖ ማለፉንም ወ/ሪት ሀመልማል ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ኮሌጁ ዛሬ በሚያስመርቃቸው ሰልጣኞች የምረቃ በዓል ላይ የዩኒቨርስቲ ምሁራን፣ ታዋቂ የኪነ- ጥበብ ባለሞያዎች የተመራቂ ቤተሰቦችና የኮሌጁ ማህበረሰቦች እንደሚታደሙም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 1464 times