Sunday, 18 September 2016 00:00

‹‹የጎደሉ ገፆች›› የግጥም መድበል ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

የገጣሚ ትዕግስት ማሞ ሶስተኛ ስራ የሆነው ‹‹የጎደሉ ገፆች›› የግጥም መድበል ከነገ ወዲያ ሰኞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በማህበራዊ፣ በፍቅርና በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ 23 ያህል ግጥሞችን የያዘው መፅሐፉ፤87 ገጾች ያሉት ሲሆን በ45 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
 በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ደራሲና ሀያሲ አለማየሁ ገላጋይ በመፅሐፉ ላይ ሂሳዊ ዳሰሳ የሚያቀርብ ሲሆን ገጣሚዋን ጨምሮ ኤፍሬም ስዩም፣ ሰለሞን ሳህለ፣ ደምሰው መርሻ፣ ባዩልኝ አያሌው፣ ምስራቅ ተረፈ፣ ምልዕቲ ኪሮስና ሌሎችም የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡

Read 1384 times