Sunday, 18 September 2016 00:00

የቀዳማዊ ኃ/ ስላሴን የስደት ህይወት የሚያስቃኘው መጽሐፍ በአሜሪካ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ በአምስት አመቱ የጣሊያን ወረራ ወቅት በእንግሊዝ አገር ያሳለፉትን የስደት ህይወት በጥልቀት የሚያስቃኘው “ኢምፔሪያል ኤግዛይል” የተሰኘ መጽሐፍ በቀጣዩ ሳምንት በአሜሪካ ይመረቃል፡፡
በቀድሞው የቢቢሲ ዋና ፕሮዲዩሰር ኬዝ ቦወርስ፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተጽፎ በጸሃይ አሳታሚ አማካይነት ለህትመት የበቃው መጽሐፉ፣ ንጉሱ በእንግሊዝ ሃገር ያሳለፉትን የአምስት አመታት የስደት ህይወት በጥልቀት የሚዳስስና በጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ነው ተብሏል፡፡
የእማኞችን ምስክርነቶች፣ ያልታዩ አዳዲስ ፎቶ ግራፎችንና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን እንዳካተተ የተነገረ ሲሆን ታዋቂው የታሪክ ተመራማሪ በመጽሐፉ ላይ በሰጡት አስተያየት፤የንጉሱ የስደት ዘመናት ህይወት ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጠው መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ መጽሐፉ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ላይብራሪ ኦፍ ኮንግረስ በሚቀጥለው ሐሙስ በሚከናወን ስነስርዓት በይፋ ተመርቆ በገበያ ላይ እንደሚውል ይጠበቃል፡፡

Read 1689 times