Print this page
Sunday, 04 September 2016 00:00

ዛሬ አዲስ ኮሌጅ 520 ተማሪዎችን ያስመርቃል

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(2 votes)

   አዲስ ኮሌጅ በዲግሪ ለ5 ዓመት በቲኢቪቲ ለ3 ዓመት ያስለጠናቸውን 520 ተማሪዎች ዛሬ በአምባሳደር ቴአትር ያስመርቃል፡፡በቲኢቪቲ ፕሮግራም በአይቲ በአካውንቲንግ፣ በሰርቬይ፣ በድራፍቲንግ፣ በኮንስትራክሽንና በኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽን ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የሚያስመርቅ ሲሆን በዲግሪ ፕሮግራም ደግሞ በአርኪተክቸርና በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና በማኔጅመንት  ያሠለጠናቸው ናቸው፡፡
የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ለማረጋገጥ በ2009 ዓ.ም የቴክኖሎጂና የቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል በማደራጀት በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም በሮድ ኤንድ ትራንስፖርትና በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና ማኔጅመንት ለመጀመር ለመንግሥት ጥያቄ አቅርቦ በመጠባበቅ ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

Read 1924 times