Sunday, 04 September 2016 00:00

የአመቱ የለዛ ሽልማት እጩዎች ይፋ ሆኑ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

   በየአመቱ የሚካሄደውና በለዛ የሬዲዮ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ብርሀኑ ድጋፌ የሚዘጋጀው የዓመቱ ምርጥ የለዛ የኪነ-ጥበብ እጩዎች ይፋ ሆኑ፡፡ ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ሽልማት ላይ በሰባት ዘርፎች ማለትም በምርጥ ዋና ተዋናይ፣ በምርጥ ዋና ተዋናይት የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ፣ የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ፣ የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም፣ የአመቱ ምርጥ ፊልምና የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ የተመረጡ እጩዎች ይፋ ሆነዋል፡፡
በየአመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይ አለምሰገድ ተስፋዬ በ‹‹እውነት ሀሰት›› ፊልም ደሞዝ ጎሽሜ በ‹‹ዩቶጵያ›› ፊልም፣ ፈለቀ የማር ውሃ አበበ በ‹‹ፍሬ›› ፊልም፣ ደረጀ ደመቀ በ‹‹አንድ ጀግና›› ፊልም፣ ሰለሞን ቦጋለ በ‹‹የፀሀይ መውጫ ልጆች›› ፊልም፣ ከሳሁን ፍስሀ (ማንዴላ) በ‹‹ሀ እና ለ›› ፊልም አማኑኤል ሀብታሙ በ‹‹መባ›› ፊልም፣ ሄኖክ ወንድሙ በ‹‹ፍቅር ተራ›› ፊልም፣ ታሪኩ ብርሀኑ (ባባ) በ‹‹ሀገርሽ ሀገሬ›› ፊልም እና አብርሀም በላይነህ በ‹‹ለኔካለሽ›› ፊልም እጩ ሆነዋል፡፡
የዓመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይት የሽልማት ዘርፍ ደግሞ በ‹‹ወፌ ቆመች›› ፊልም ፍርያት የማነ፣ በ‹‹መባ›› ፊልም እድለ ወርቅ ጣሰው፣ ብርቱካን በፍቃዱ በ‹‹የፀሀይ መውጫ ልጆች›› ፊልም፣ ቃልኪዳን ጥበቡ በ‹‹እውነት ሀሰት›› ፊልም፣ ሀናን ታሪክ በ‹‹ለእኔ ካለሽ›› ፊልም፣ ሰላም ተስፋዬ በ‹‹አንድ አፍ›› ፊልም ሄለን በድሉ በ‹‹የአራዳ ልጅ›› ፊልም፣ አዚዛ አህመድ በ‹‹መንሱት›› ፊልም እና ዕፀህይወት አበበ በከዕለታት ፊልም እጩ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም ዘርፍ ደግሞ የልጅ ሚካኤል ታዬ ‹‹ዛሬ ይሁን ነገ››፣ የሳሚ ዳን ‹‹ከራስ ጋር ንግግር››፣ የአብዱ ኪያር ‹‹ጥቁር አንበሳ››፣ የፍቅር አዲስ ‹‹ምስክር›› እና የኤፍሬም ታምሩ ‹‹እንደገና›› ተመርጠዋል።
በየዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ የሳሚዳን ‹‹ጠፋ የሚለዬን›› የዳዊት ነጋ ‹‹ወዛመይ››፣ የእሱ ባለው ይታዬው ‹‹ማሬ ማሬ››፣ የዓለምዬ ጌታቸው ‹‹ዋሸሁ እንዴ››፣ የጃኖ ባንድ ‹‹ይነጋል›› እጩ ሆነዋል፡፡
በዓመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ ዘርፍ ሚካኤል ታዬ (ልጅ ሚካኤል)፣ ሳሚ ዳን፣ ብስራት ሃ/ማሪያም (ቤሪ) እና ራስ ሙሌ ተመርጠዋል፡፡ የዓመቱ ምርጥ ፊልም ተብለው በእጩነት ከቀረቡት ውስጥ ‹‹የነገን አልወልድም››፣ ‹‹ሀገርሽ ሀገሬ››፣ ‹‹ወፌ ቆመች››፣ ‹‹ሀ እና ለ›› ‹‹ዮቶጵያ››፣ ‹‹እውነት ሀሰት›› ‹‹የፀሀይ መውጫ ልጆች››፣ ‹‹አስታራቂ››፣ ‹‹መባ›› እና›› ‹‹የአራዳ ልጅ›› ፊልሞች በእጩነት ተመርጠዋል፡፡
በየዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ ስር፣ የሳሚ ዳን ‹‹ጠፋ›› የሚለዬን፣ ‹‹የፍቅር አዲስ ነቅአጥበብ ‹‹ምስክር›› ፣ የወንድሙ ጅራ ‹‹አንድ ቦታ››፣ የአብዱ ኪያር ‹‹ዥዋዥዌ›› እና የሄኖክ መሃሪ ‹‹እወድሻለሁ›› የተሰኙት ቪዲዮዎች በእጩነት መቅረባቸውን አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡

Read 3989 times